ምንድራሺው ቑንዚ

ዘውዴ በካሉ

ወባ አኹኪ ምንድራሺው ቑንዚ ይቶፒያዳ ኩል ዙራሙሪዳስታ ኩላዲሪኺዳ እሳንስ ካንትስታው ቑንዚያኽ:: እን ቑንዚ አጌራው ይኮኖሚዳ ኬፍቲኔ ቻኒስቶ ታምፃማጊ አግስቴ:: ወባው ቑንዚ ድሚ ብሪዳ ናቔማ ዝኮው እልስ ካንትስታቲው እንኪቲኒያኽ:: ወባው ቑንዚ እልስ ካንትስታቲው ፕላዝሞዲየም እስታንኩ ቑንዜ ፌያፌይጝፃንኩ እንኪቴንካስ ይንታው ቑንዚያኽ:: አቒዴስ አቒሾ ፌያፌይጛው ምንድራሺት ሚቒያስ ያኹስ ክልልኻዳ ወባው  አኹኪ ምንድራሺው ቑንዚስ ጉሽፅካ ፕላዝሞዲየም ፋልሲፈረምስታ ፕላዝሞዲየም ባይባክስያኽ:: እን ቑንዚ ምንድራሺት ሚቓያስ አቒዴስ አቒሾ ፌያፌይጛው ያኹስ ሜስኬሩምዴስ ቴሳሶኺስታስታ ማንዚዴስ ሴኔኺስታ ዝኩንኩ አርፍካዳ ሚንቺትስ እሳንጜ::

ምንድራሺው ቑንዚስ እምስትኹ አቒዳ ካንትስታንኩ ምልኻትካኪላ፡- አካላት እንኩዊንትጝ፣ እኹማ እኹማ ፄውጝ፣ ጛሬ ቑንዳፅጝ፣ አካላትኩ ታምትጝፅካዳ ቑንዚው እንኮኽሰት ዝኩጝ፣ ምግቡ ፋይ ኔኬትጝ ቑንዚኩ ምልኻትካኽ:: እምፕል አቒ እኒጛ ቑንዚኩ ምልኻትካ ካንትስቱኒዴስ እክምኒውሳ አግልግሎቴ አግፃውላስ ይጉኒጊ ዴሜካ ቑንዚ ይዝኩዌማ ቑንዳስትኹ አቒ ጛሬ ካላማ እንዜጝⶓ አኹኪ ልቕልቕ ንⶓ አቲጝ፣ ትራኹፅጝስታ ኬውጛ ጋቲታ ጃላፅጝ፣ ብሪው እንፂጝስታ አንኮሌ ዜኔግጝ ካንትስቴ:: ጋያኪ እምቢት ናማ እክምኒውሳ አግልግሎቴ አግፃውላስ ይጉኒ ክርጝስ ካሌ::

ወባውሳ አኹኪ ምንድራሺውሳ ቑንዜ ካላካልጝስ ፄውጝ ዝኩክ ቤዴራ ትንካክካኪላ ዝኩና:: እኒጛኪላ ዙራሙሪዳ አግስታንኩ አኾ ቲሪፃንኩ አኹኪ እሜንኩ አክኽካዋ ዱንፅጝ፣ ፍሮ ዴፌንጝ፣ አጐበሮ ቱስቲስ ቴኬምስትጝ፣ ጝናኻዳ ኬሚካሎ አሬችጝ፣ ወባው ቑንዚኩ ምልኻትካ ካንትስቱክ አቕ እምቢት ንካማ ቲኑ ጉትፕሾ ካሳማ ምርማሬ ፄውጝስ ምንድራሺው ቑንዚዴስ ካላካልጝስ ካሊስቴ::

አማኻሪ ክልሉ ቲኑ ቢሩ አቕፅኹስታጊ ክልላኻዳ 82 ትኩሚ 5 ያኻንኩ ኬቤልካ ወባው  አኹኪ ምንድራሺው ቑንዚ ሚንቻኩ ዙራሙርካኽ:: አማኻሪ ክልሉ ቲኑ ቢሩ ቲኖ ማንዲጙ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መልሰው ቻንያለው ክልልዳ አግስታንኩ ቲኖ ማንዲጝስታ ወባውሳ ቑንዜ ካላካልጚውስታ ቼፍጝጚኩ ውማይቴንካሊ ባርዳርዳ ፄውኑ ኩስጚዳ ወባ እሳንጛማጊ አኽⶓ ጌሌፅካ:: አቶ መልሰው ወባው ቑንዚ ጊዝዴስ ጊዞ ዴሜካማጊ ይንትኹ አኽጝስ እምፕልታቕ ወባዋ ካላካልጚውሳ ሴሎ ቱስቲስ ቴኬምስትጝስ ጚጛርጛሳስታ ዙራሙሬ ማንዲጝ ቱስታው አኹኪ ፋይፃው አኽⶓ ጌሌፅካ::

ሜስኬሩም 21 ጌርክዴስ ቴሳስ 22 ጌርክ 2016 ም.አሜቶኺስታ ብሄራዊ ወባው ሶኼት እስታማ ኬቤርስታው ያኹስ ቲኑ ቢሩ እርዳታንኩ ትኩታኩ አካልካሊ አኽጝስ ወረርሽኞ ካላካልጚስስታ ቼፍጝጚስ አሬባሬብጜ ፄውካማጊ አኽⶓ ቶኬምካ::

ክልላኻዳ ሚንችካ ዙራሙርካዳ ወረርሽኙ ፄጌርስ ኬሴትስታማ እምፕልታቖ ኬፍንኹ ቑንዚስስታ ክርጝስ ታምፃማጊ አኽⶓ ዙሙንኩ አቶ መልሰው ወባዋ ካንትኹስ  ቴርቱንኩ  ምልኻትካዋ ክንቲ ጝናዳ አግስታንኩ ሚኒ-ሚዲያስታ ፀረ-ወባኩሳ ክቤብካዋ ቴኬምስታማ ወባው ካላካልጚስታ ቼፍጝጚዳ ትኩትኹሳ እንፅኼንቶ ፌያፌይጝፅጝስስታ አጐበር ቴኬምስትⶓ ካንትፃውሳ ሞዴሎ ቴርሳማ ሼውቴ ፌቴርጝ ፋይፃው አኽⶓ እርዳትፅካ::

አዊ ብሄረሰቡ ቺፅጝፂው ቲኑ ሜምሪው እዝቦ ጉዳንኩ ቑንዝካው ካላካልጚው ውማይቲኒ አቶ የኔው አላምረው አዊ ብሄረሰቡ ቺፅጝፂታጊ ምንድራሺው ቑንዚ እስንጛማጊ አኽⶓ ጌሌፅካ:: ምንድራሺው ቑንዚ አሜትዴስ አሜቶ ዴሜካማጊ አንትⶓ ድኹንኩ አቶ የኔው 2014/15 ም.አሜትዳ ሊኽዴስ 82 ታፋ ያኻንኩ አቕ ቑንዚስ ፂኪስትⶓ ጌሌፅካ:: እን አሜትስ ዴሜካ 2015/16ው ኩርማን አሜትዳ ምንድራሺው ቑንዚው እሳንጚ ካንትስታኒ 25 ሸይ ዴስ ጃላ ያኻንኩ አቕ ቑንዚስ ፂኪስትⶓ ድኹዌካ:: ብሄረሰቡ ቺፅጝፂታጊ ምንድራሺው ቑንዚ እሳንጛንኩ አኹኪ ሚንቺትስ እሩባኩ ዋልታ ወረድካስ አጐበር እይስታታ፣ ኬሚካል አሬችስታታ፣ ዙራሙሬ ፃንኩፃንታ ሼውቴ እይጝስስታ ቱስቲስ ቴኬምስታንታ ዋሴንስትⶓ አቶ የኔው ዙሜካ:: ምንድራሺውሳ ቑንዜ ካላካልጚውሳስታ ቼፍጝጚውሳ እንፅኼ ዙራሙሪ ቺፋ እንፃኽስትጝስስታ ቲንኩሳ ውማይቴንካዋ ሴሌቴንፃማ እንፅኺሾ ቱጝስ ክልልታጊ ኬሴትስትኹ ሰላሙ ችግር ፅንጋኻ አኽⶓኪላ ጌሌፅካ::

ብሄረሰቡ ቺፅጝፂዳ ምንድራሺው ቑንዚ እሳንጛኩ ወረድካ ክቻዴስ አዩ ጉዋጉሲ ወረዳ፣ ቻግኒ ኬቴም ቺፅጝፂ፣ ጉዋንጉዊ ወረዳ፣ ዚጋሚ ወረዳ፣ ዳንግሊ ኬቴሙ ቺፅጝፂስታ ጃዊ ወረዳ አኽⶓ ጌሌፁንኩ አቶ የኔው ጃዊ ወረዳዳ ቤክተርሊንክ እስታው ፕሮጄክት አሜትቺፋ ኬሚካሎ አሬችፃማጊ ቑንዚው እሳንጜ ኔኬትⶓ ጌሌፅካ::

2016 ባጄት አሜትስ ምንድራሺው ቑንዚ እሳንጚው ምክንያትስ ፌይኹ አሜትዳ ላጛ ወረድካዳ አሬችስታሺኹ ኬሚካል 2016 ም.አሜትዳ እሪ ሚንቺጙ ምክንያትስ ምንድራሺው ቑንዚ ሚንቺጝስ  ሴዛ ወረድካዳ 13 ኬቤልካዳ ኬሚካል አሬችስታታ ቤዴራ ቴርት አሌድስትⶓኪላ ድኹዌካ::

ወባው አኹኪ ምንድራሺው ቑንዚ እሳንጛው እንኩዊንት ሚንቻው ወክትዳ አኽⶓ ጌሌፁንኩ አቶ የኔው ቑንዜ ካላካልጝጚስስታ ቼፍጝጚስ ዙራሙሬ ፃንኩፅጝ፣ ኩሬ አኹኪ አኾ እሜንኩ ኮርሻማርሽካዋ ዱንፅጝ አጐበሮ ቱስቲስ ቴኬምስትጝስታ ቑንዚው ምልኻት ካንትስታኒ እምቢት ናማ ቲኑ ጉትፕሾ አኹኪ እክምኒው ኾትሾ ካሳማ ማራማርስትጝስ ካላካልጝስ ካሊስታው አኽⶓ ዙሜካ::

ምንድራሺው ቑንዚ አማኻሪ ክልልዳ ናማኪ ብሄረሳቡ ቺፅጝፂዳ ፌይኹ አሜትዴስ ኬፍንኹ አችስ እሳንጛማጊ ይንትⶓ ሲፋማ እንሳ ቑንዜ ካላካልጝጚስስታ ቼፍጝጚስ ፄውጝ ዝኩኹስ ቤዴራ ቴርቶስታ እይስታውሳ እክምኒውሳ አግልግሎቴ ካንትኹስ እክምኒው ውማይቲኒ ንባርካዋ እያ::

ዶ/ር መኮነን ምናየሁ ትክላሊ አኪም ያኻኒስ ምንድራሺው ቑንዚ እሳንጛው ችኽ ፉስስታ ችኽ ቱስ አኽⶓ ጌሌፅካ:: ምንድራሺው ቑንዚ ችኽ ቱስ እሳንጛውዴስ ጃላ ችኽ ፉስ ሚንቺትስ እሳንጛንኩ አኽⶓ ጌሌፅካማ ችኽ ፉስ ሚንች እንኩዊንት ዴሜካማጊ ይንታው  አኽⶓኪላ ጌሌፅካ::

ምንድራሺት ሚቓያ እሩብጝስ እንኩዊንት፣ ቲሪኹ አኹ፣ ፃሚ ዲብስታ እሊኩ ሱኻንት ዝኩክ ዲብካዳ አኽⶓኪላ ዶ/ር መኮነን ድኹዌካ:: ምንድራሺው ቑንዚ ወባስ ቑንዳስትኹ አቒዴስ ቲንዌና እቒሾ ቑንዜ ፌያፌይጝፅጝስ ኹና ምንድራሺት ሚቓያዳ አግስታው ፕላዝሞዲየም እስታው እንኪቲኒስ  ይንታው አኽⶓ ጌሌፅካ::

አሌምዳ ምንድራሺውሳ ቑንዜ ያጋንኩ አንኩዋ ፕላዝሞዲየምካ ዝኩንኩ አኽⶓ ጌሌፁንኩ ዶ/ር መኮነን አጌራኻዳ ዴሜካ ሴዛ ያኹኒኪላ ቑንዜ ፌያፌይጝፃንኩ ላጛ ፕላዝሞዲየምካ አኽⶓ ጌሌፅካማ ፕላዝሞዲየም ፋልሲፈረምስታ ፕላዝሞዲየም ቫይቫክስ አኽⶓ እርዳትፅካ::

ፕላዝሞዲየም ፋልሲፈረም እስታው ምንድራሺው ቑንዚዴስ  ቢቻ ወባ እስታማ እቑስታው ያኹስ ቑንዜ ፌያፌይጝፅጙ አክም ሊኽዴስ 60 ታፋ ያኹስ ፕላዝሞዲየም ቫይቫክስ ዴሜካ ሊኽዴስ 40 ታፍ አኽⶓ ዶ/ር መኮነን ጌሌፅካ::

ምንድራሺው ቑንዚ ሚንቻው ኩልስታ ኩላ ዲሪኹ ዙራሙሪዳ አኽⶓ ጉሽንኩ ዶ/ር መኮነን ችኽ ቱስስታ  ችኽ ፉስ ሚንቺትስ ካንትስታው ያኹስ ምንድራሺት ሚቓያ እምፕሎ አቔ እጝቱኒዴስ ላጛ ሶኼትዴስ ፋሌንጋ ምልኻቶ ካንትፃው አኽⶓ ድኹዌካ:: ወባው ቑንዚ እሚኩ አቕዳ ካንትስታው ምልኻት ቑንዚው አይኔትታ ሊሊቲ ያኹኒኪላ እንኩዊንት፣ እኹማ እኹማ ፄውጝ፣ ጛሬ ቑንዳፅጝ ዝኩኽ አኽⶓ ጌሌፅካ:: እን ቑንዚ ታይፎይድሊስታ ታይፈሱ  ቑንዚሊ ፄጌርጝፃው ፅኹር ዝኩኹ አኽጝስ ምልኻትካ ካንትስታኒ እክምኒው ኾትሾ ካሳማ ቼሜትጝፅጝ ፋይፃው አኽⶓኪላ ጌሌፅካ::

ፕላዝሞዲየም ፋልሲፈረም እስታው ምንድራሺው ቑንዚ አቒው ብራኻ ቱኒዴስ ፋሌንጋ አካላታኻዳ ዝኩኹሳ ግሉኮሶ አኹኪ ብሬ እንፂሳው፣ አካላታኻዳ አሲዶ ሚንቺሳው ያኹስ እኒጛ ቑንዝካ አካላቶ ዴሬፅካማ ክርጝስ ታምፃና::

እን ቑንዚ አንኮሌ እሚው አኽⶓኪላ ዶ/ር መኮነን ጌሌፅካ::

አብን

AMECO Cherbewa