ፍትሬት አብቱ እንፅኺ ኽሉቺፋሱ ቴግባር

ታደለ አጋጄ

 

ዊዳፊ ፍትሬት አብቱስታ ቴፋሴሱ ልማቱ እንፅኺ እምፕልታቕ ቴኬምስታንታ ፄውጝስ፣ ጌፄሩሳ ግብርኒውሳ እንፅኼ ስራ ፄውኹሳ ልማቱ ስትራቴጄ ሲፍጝስ፣ እንግራ ይጉዊ አሬስጙሳ ሴሎ ኪስጝስስታ ኬፍቲኒ አችስ ጉዲስትኹሳ ብቴ እሺኹሾ ዙራታ ፄውጝስ ኬሽኹ ዳብዚ እንኩርስታማ ቴግባርሾ ቱስታ::

አምሉ ኢኮኖሚው ልማትዳ ስርትኹ፣ ሚንችካ አሜትካዋ ጉዲስታማ እሺኹሳ ብቴ እሺኹሾ ዙርፅጝስ አሜት ቺፋ ሚንችካ ዙራሙርካዳ እምፕልታቖ  አሴቴፍጝፅጝስ ፍትሬት አብቱ ማንዲጚው እንፅኺ እንፃኽስስታማጊ አግስቴ::

ፌዩንኩ አሜትካዳ እንፃኽስቱንኩ ኽብፂውስታ አኾ ማንዲጚው እንፅኺ ጉዲስትኹሳ ብቴ ዙራታ ፄውጝዴስ ድምክና ፍትሬት አብቱሳስታ    ቴፋሴሱ እንፅኽካ አብቱ አግፅፂ አኽጝዴስ ፌያማ ጌፄሩ ዙራሙሪዳ እንፅኺው ድል ፌቴርስታታ ፄውጝዳ ኬፍቲኒ ትክም ዝኩኽያኽ::

ፍትሬት አብቱስታ ቴፋሴሱ ልማት እንፃኽስስቱንኩ ስፍርካዳ እንሴስካዋ ዴሌብፅጝ፣ ቴክልካዋስታ ኩፓኩፕካዋ ሊሚፅጝስ፣ ፅኻራዋ እሩብፅጝስስታ ዴኑ ልማትስ እምፕልትቕ ቴኬምስታንታ ያኼካማጊ አግስታና::

ፍትሬት አብቱስታ አኾ ማንዲጚው እንፅኺስ እንፃኽስቱንኩ ቴግባርካ ክርፄ ዋይሜ ሜዜጌብፁኒውላ ዳንጉንካኪላ ካንትስታና::

እምፕልታቕ ፍትሬት አብቱ ልማቱ እንፅኺ ዝማቺ እንፅኺዴስ ፌያማ ጌርክቺፋሱ እንፅኺ ፄዋማ እንፃኽስትጝስ ዋሺኒኪ ጊዝካስ ሊሊቲ ትኩትስ እንፃኽስትጝስ ምርቶስታ ምርታምቶ ሌጌፅጝስ ፍትሬት አብቱስታ አኾ ማንዲጚውሳ እንፅኼ እልዉኒዉ ጉዳይ ፄዋማ እሚጝ ፋይፃዊያኽ::

ንጙዊኒ ቴፋሴሱ ልማቱ እንፅኺ ትር 15 ጌርክዴስ ጄሜራማ እንፅኺ አኮሜችስታማጊ አግስቴ:: አዊ ብሄረሰቡ  ቺፅጝፂዳ ሊሊትጙንኩ ወረድካዳኪላ ፍትሬት አብቱስታ ቴፋሴሱ ልማቱ እንፅኺ ይስጛማ ሲፉታኽ:: ጉዋንጊ ወረዳዳ 2016 ም.አታስ ፍትሬት አብቱ ልማቱ እንፅኼ 18 ኬቤልካዳ እንፃኽስስታማጊ አግስቴ:: 58 ቴፋስስኩ ስፍርካዳ 800ዴስ ጃላ ቴክኖሎጅካዋ ቴኬምስትጝስ ቴግባራዋ ፄውጝስ አኬድስታ::

ጉዋንጊ ወረዳው ግብርኒው ፅፌትጝናሱ አላፊ አቶ አበባው አምሳል እንዴስ ቤዴራ እንፃኽስቱንኩ ኽብፄስታ አኾ ማንዲጚው እንፅኺ ክርፄ ዋይሜ ሜዜጌብፅⶓስታ አሬሳቻንትካዋ ቴኬምስታንታ ፄውⶓ ቶኬምካማ እንፃኽስትኹ ፍትሬት አብቱ ልማቱ እንፅኺስ ትክልትካዋስታ ኩፓኩፕካዋ ሊሚፅጝስ፣ እንሴስካስ ያኻውሳ ክዮ ዋግፅጝስ፣ ክምካዋ ቡዚስጝስስታ ፅኻራዋ እሩብፅጝስ አሬሳቻንትካ ትክሞ አግፁንኩ አኽⶓ ዙሜካ::

እንዴስ ቤዴራ ጉዲስታሺኹስታ ሴብሎ ዋግፃቲው እሺኹ ብቲ እንፃኽስትኹ እንፅኺሳ ናኪኒ ዎክትስ ኬሽኹስ ምርቶ ዋግፃማጊ አኽⶓ ዙሙንኩ ግብርኒው ፅ/ጝናሱ አላፊ እንዴስ ቤዴራ ካጋሺንኩ አልካስታ ብንካዳጊ አኾ ካንትናናጊያኽ ንካ::

ጉዋንጊ ወረዳታ ቴፋሴሱ ልማቱ እንፅኺ ይማሊ ኬቤሊዳ ፄውስትኹ ጄሚርፂ ቴርትዳ አግስቱንኩ ጉዋንጊ ወረዳው ቺፅጝፃንቲ አቶ ሰለሞን ቦጋለ ፍትሬት አብቱ ልማትስታ አቒው ይዎት ጎሌልጛቲንኩ አኽጝስ እምፕልታቕ ሰላማዊስታ ልማታዌ አኺኒስ ጉድ ልቕልቕቲስ እንፅኺሾ ቱⶓ ዙሜካ::

“ባግትኹሳ ብቴ ክምንትስ አሬኬብፅናላኽ” ኑንኩ ጉዋንጊ ወረዳው ቹዋ ቺፅጝፃንቲ አቶ ሰለሞን ቦጋለ ወረዳው እዝብ ዙራሙሪውሳ ሰላሞ ማንዲፅጝስ ሚንችካ ኬቤልካዳ ቴፋሴስኩ እንፅኽካ 20 ሲፍጝጚኩ ጌርክካስ ይስጙኽ ዳድስ እንፃኽስስታንኩ አኽⶓ ዙሜካ::

አዊ ብሄረሰቡ ቺፅጝፂው ግብርኒው ሜምሪው አላፊ ዶክተር ታደሰ አስፋው 2016 ም.አሜታዳ ብሄረሰቡ ቺፅጝፂታ እን አሜትስ 310 ቴፋስስካዳ ፃምርትጙኽ ኽብፂውስታ አኾ ማንዲጚው እንፅኺ እንፃኽስስታማጊ አግስታው አኽⶓ ጌሌፅካ::

አይር እግልታው ኪሲስ ፂኪስዉታሳ አምሉ ኢኮኖሜ ሌጌፅጙ ግብካዋ አኬዳማ እንፅኺሾ ቱስቱኒዴስ 10 አሜታዴስ ጃላ ቼፍፅኹ ፍትሬት አብቱስታ አኾ ማንዲጚው እንፅኺ እምፕልታቖ ፍትሬትሊ ማልጜ ፃምርሳ::

ፌዩንኩ አሜትካዳ እንፃኽስስቱንኩ ፍትሬት አብቱስታ ቴፋሴሱ እንፅኽካስ ኽብፂው አሉምትዳ አግስትኹ ኪሲዴስ ፌያማ ብሄረሰቡ ቺፅጝፂዳ ዴኑ ሽፋን ሊኽዴስ 40 ታፋሳ ኬፍናታ እርዳትኹ አኽⶓኪላ አዊ ብሄረሰቡ ቺፅጝፂው ግብርኒው ሜምሪው አላፊ ዶ/ር ታደሰ አሰፋው ዙሜካ::

ንጙዊኒ ፃምርትጙኽ ቴፋሴሱ ልማቱ እንፅኺስ 310 ቴፋስስኩ ስፍርካዳ እንፃኽስስታው ያኹስ 125 ሻይዴስ ጃላ አሬሳቻንትካ  እንፅኺዳ አሴቴፍጛንኩ አኽⶓ ግብርኒው ሜምሪው ንባር ቶኬሜ::

አማኻሪ ክልልታ  ዴሜካ እምስትኹ ሳኑ አርፍካዳ 376 ሻይ ሄክታርዴስ ጃላ ብቲዳ ፍትሬት አብት ልማቱ ማንዲጚው እንፅኺ አኮሜችስታው አኽጝ ጌሌፅስታ::

ክልሉ አችስ ፍትሬት አብቱ ማንዲጚው እንፅኼ ተሁላደሬ ወሪዳዳ ጄሜርፁኑ ጊዝዳ አግስቴካማ ዙሚትጜ ፄውንኩ አማኻሪ ክልሉ ግብርኒው ቢሩ አላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) ፍትሬቱ አብቱ ልማቱ እንፅኺ ሳኑ አርፍካዳ ሊሊቲ ትኩት እይስታማ እንፃኽስስታው አኽⶓ ዙሜካ::

ፍትሬት አብቱ ልማቱ እንፅኺ ጎሌልስቱንኩ 9 ሻይ 60 ቴፋስስካዳ 376ሻይ ሄክታርዴስ ጃላ ብቲዳ እንፅኼ አኮሜችስታማጊ አኽⶓ ዙሜካ::

እን እንፅኺዳኪላ ሴዛ ሚሊዮንዴስ ጃላ እምፕልታቕ አቺትጙኹ ዳድስ አሴቴፍጛንኩ አኽⶓ ዙሜካ::

ኽብፄስታ አኾ ማንዲጙ እንፅኺዳ 376 ይ 561 ሄክታር ብቲዴስ 234 ሻይ 118 ሄክታር ብቲ እስካዊስ፣ 142 ሻይ 443 ሄክታር ብቲ ዴሜካ እጂኹ ቴፋሴሱ ልማት እንፃኽስታው አኽጝ ጌሌፅስታ::

ፍትሬት አብታሳ ማንዲጝስታ አንካባንኬብጝ እምፕላ አጌራው ልግስስ ቹዋ ጉዳዬኽ። ፍትሬት አብታሳ ቱስቲስ እሜውላ ይጉጝ ዴሜካ ኽብፂ ኩሪስ ሻራሻርስታማ ካሳታ ፄውጝስ ብቲ አሬ ዋግፃቲታ ፄዌ።አየሩ አኺኒ ዛቢትጚ ኬሴትስታማ ቤሬኽትስታ ባግት ፌቴርስቴ። ፍትሬትኩ ማድንካዳ ጉዳት ታምቤ። ፍትሬቱሳ አብቶ ቱስቲስ እሚጝስታ አንኬባንኬብጝ ምርቶስታ ምርታምቶ ሌጌፅጝስ፣ አይሩ እግልታ ክቼማ ባግት ቤሬኽት ኬሴትስታቲታ ፄዌ። አጌራውሳ ፍትሬቱሳ አብቶ ማንዲጝስ ሊሊትጙንኩ ስፍርካዳ ቴክልካዋ ቴኬልጝ ምንግስት እይኹ ሊሊቲ ትኩትስ ዜርፋ ሚንቺ እንፅኺ አኮሜችስታ። ችኹ ወክትዳ እንፃኽስታው አምሉ አሻሪው ሜርሃ ግብር አጌርታ ኬሽኹ እንፅኺ አኮሜችስታ። አጌሩ አችስ ፍትሬቱ አብቱ ልማቱ አንኬባንኬብጚ ይስጙኽ ደድስ ሲፍጝ ኽስኹስ ምርቶስታ ምርታምቶ ዴሜኬ። ችግኞ ቴኬልጝስታ ካዌኖ ማንዲጝ ፣ብቲ ኩሪስ ሻራሻርስታቲታ ፄውጝ፣ፍትሬትኩ ማድንካ አኹስ ቑፅስታማ ካሳቲታ ፄውጝስ ኬፍቲኔ ፍሼ ፄዌ። እንሳ ይስጝፃማ ሲፍጝ አጌራስ ሚንች ትክም ዝኩዋታ ፄዌ። አኽጝስኪ ፍትሬት አብቱስታ ቴፋሴሱ እንፅኼ እልዉኒዉ ጉዳይ ያኻማ ሲፍጝ ቱስቴ::

አብን

AMECO Cherbewa