ይቶፒያው ታሪክዳ አሻሬ እንኩርኹ ሴሌቴንፃንቲ

ታደለ አጋጄ

ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው ይቶፒያው ልኩ ኩታው ታሪክዳ ኽሳንቴ አሻሬ እንኩሩንኩ ውማይቴንካዴስ እምፕልያኽ:: ይቶፒያ ቲሪትጝፂኹ አፍሪካው ዋንቺዳ 31 አሜታዴስ ፋሌንጋ ልኺትጚዉ ሜድሬኽሾ ዙርታታ ፄውንኩ ውማይቲኒ አኽጝስ ታሪክ ዜኔጋላ::

ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው ጌሌፁኑውስታጊ አሌሙ ልኩ ኩታ አብቱ ጊሊፂስታ አጌርካው ፖለቲካው ካንትፂ አኽⶓ ጄሜሩኒዴስ ሚንችካ አሜትካዋ ቼፍፅⶓ ዙሜካ::

ይቶፒያ ልኩ ኩታው ችግርካ ሌጌሳ ታምብካዋ ሌጌፅጝዳ፣ ዜርፍዳ ካንትስታው ዜሮ ጎሌልጙ፣ ስፖርቱ እንፃኽፂ ስፍርካ ዳላው አኺኒስ እላቲንኩ አኽጝስታ ውማይ ዌና ያኹኽሳ ጉስስትጙ ችግር አቕት እላቲኩ ሴሌቴንፃንትካስ ጉስስትጝ ልኩ ኩታዳ ካንትስታንኩ ችግርካ አኽⶓ ጉሽካ::

እን አጌራውሳ ልኩ ኩታ ሌጌፅጝስ ፋኑስ እሊኩ አጌርካው ልኩ ኩታዋ ዋትጛ ሌጌፁኑ ናማ ካሲⶓ ፋያውስታ ልኩ ኩታው ውማይቲኒ አምንስታንቶስታ ጌሬትቶ ካሴው አኽⶓ ቶኬምካ::

ብሄሪዊው ኬች ዳላው ሴሌቴንፅጙ ካሌቕትስታ ዴስ እላቲንኩስ ጉስስትጝ አጌራው ልኩ ኩታዳስታ ዴጌፋንትካዳ ኬሌድጝ አኽⶓኪላ ኽይትጝፄካ::

ሚንችካ አጌርካ ልኩ ኩታስ ሌጌሳ ታምብካዳ እንፃኽስትጝስ ዋይሚስታ አኽⶓ ጉሽካማ እን አጌራዳ ኩፅኒ ሚንች ጌንዜብ ፋማጊ ዋይሚስታ አኽጝ ካሊስታያሱ አኽⶓ ዙሜካ:: ናካዳ እንፃኽስስታማጊ ዝኩኽ እንፃኽስትጝጜ ዋይሚስታ ፄዋውላ ይጉኒ እሊኩ ዴስ ዝኩኽ አጌርካውሳ እንፃኽስትጝጚ ሲፍጝ ቱስታው አኽⶓ ጉሽካ::

እን አጌራው ልኩ ኩታው እንክራንትካ “ፕሮፌሽናል” አኽጝስ ካሌካያሱ ምክንያቲ ልኩ ኩታዳ ቴጌቤርስታማጊ ዝኩክ ክችክቻ ጋቲው አኽጝስ አኽⶓ ታክስፅካ::

አብን

AMECO Cherbewa