ከረከረተ ፅውዘ ባክቴሪያዝጘ፣ ቫይረስዝጘ፣ አልተተ ተሕዋስያን ዊንም ፈንገስዝጘ የቁ ረቂቅ ተሕዋስያኒዝጘ የቁ ፅጎቁ ፍጥረኒዝ የጝ ተረውድ። ላው እጅሪስ ላዘይዝጎ፣ እንሰሲዝ ዊንም ላዘ ኻቨረ ገቨይዝ፤ ቺተቺተው ጉግዝ እጅሪስ እጅሪዝጎ ጭቅተዝ ዊንም ጅልውልወዝ ትኒተው ቕጅወም የጝ።
እቀጘዝ አርቕሽተቊ ከረከረተ ፅውዘ ማኽሊስ ግፈ፣ ኢንፍሉዌንዛ፣ ኮቪድ-19፣ ኢቦላ ፣ ሄፓታይተስ ፣ ኤችአይቪ/ኤድስ ፣ ሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ ኢንፌክሽን፣ ፖሊዮ ዝመ ዚካ ቫይረስ ቓሊሰንጥ ጛይ።
ኤች ኤይቪ፣ ሄፓታይተስ ቫይረስ ስመ ላጥም ዊስቭትዙ ዲምቅሽንዝ ከረከረቁ ፅውዘንጥድ አልም አቅቨ ተግዝ እቀ ኽቭር አቕቨ ትኽነይል ችግሰ አቐነውድ WHO አርቒስኩ፡፡
እንዛይ ፅውዘንጢስም አምረዝ 2 ነቁጠ 5 ሚሊዮንዝ ንየ እቅ ጝታ ሩሔድ በቁ አጘጘ ድርጅትድ ፊሰው ሪፖርትድ ቓሊሰኩ። እን ትኽነዙ ችግሰድ አጉረውዝ ትኒትን ፃየቁ ይሽትጝ ኻስቭሸቁ ኻግራንድ 2030 ፅውዘይዙ ትኒትንድ 7 ነቁጠ 8 ይዝ 0 ነቁጠ 7ይዝጎ ቃፅቨናንስ አልም አቅቨ ትኽነዙ ድርጅትድ ኻለይ ፃይ ፍልውልዋጙ አቐነውድ ጋልፅኩ።
ዲቈው ፈረንጀኒዙ አምረይዝ ሳይፊሊስ (SYPHILIS) ይሽት ጭጝሸው ዊስቭትዝ ከረከረው ቫይረስ 15-49 እድሚል ችጝሸቁ ላው ሚሊዮን እቅ ጠቃዝኩ። ተረቲዝም ሰውጠ ሚሊዮኒዝጎ እግዘድ ቈሽጠ ቸለንትጘ ጋልፅሽተው አቓንድ፤ ትኒትንድም አሜሪካስመ አፍሪከት ኻግራኒል አጉረተ ችጘር ፃየነውድ ጋልፅሽትኩ።
1 ነቁጠ 2 ሚሊዮን አልተቁ አይርዝ ሄፕታይተስ ቢ፤ ላው ሚሊዮን አልተቁድ ቈሽ ሄፕታይተስ ሲ ጠቃሸጥ አቕጝ ሚዝግቭሽጝኩጙ፡፡ ውርም ፈኑ ማኽተነ፣ምርመረዝመ ኽክምነዙ መሰሪየን ፅብጝሽም፤ ሄፕታይተስዙ ቫይረስዝ ክረቁ እቂዙ ንቕፀድ 1 ነቁጠ 1 ሚሊዮኒስ 1 ነቁጠ 3 ሚሊዮንዝጎ ንየስ የውኩ።
ኤች.አይ.ቪ.ኤድስት ሚሪሸውዝ 2020ዝ ዊነው 1 ነቁጠ 5 ሚልዮኒዝ 1 ነቁጠ 3 ይዝጐ ሳስ ሸነው ቸልሽሽም፤ ጥቅለ ኽዝቪጅቅ ቓልሽታንድ ላውላው ጅውንጢል ኤች.አይ.ቪ አጉረውዝ ትኒተነውድ ጋልፅሽትኩ፡፡
ንጭቱ ይና ዲቭየይዝ ወይ ኽምረ ብሔረ እቅ ጭሰጭሰን ድሃነ ወረደ ትኽነ ኻይን ጽ/ጝን ቲክነተ ዲቈተ አቐቊ አት አበበ አዛኔጅቅ ከረከረተ ፅውዘዝ ጅሉዘ ፃቭነው ዊንተድ አንቭቭስነ ቀኑን።
ከረከረተ ፅውዝጥ ወረጘዝ ተርጘኩ?
ባክቴሪያዝ፣ ቫይረስዝ እንዝጘም ፈንገስዝ ተርጘኲ።
ከረከረተ ፅውዝጥ ጎነ ምላሰንድ ወረጘ አጠ ቸለኩ?
እምቘዝ፣ አየርዝ ዊንም ዳቐዳቕሸነውዝ ተረቁ ጛይ። ጝታ ላው ላውድ ቓልናንድም፦
ባክቴሪያዝ ተረቊ፦ አየርዝ ከረከረቊድ ሲብዙ ምች፣ ሲብዙ ነቀርሰ፣ ቀርዝዙ ፅውዘ ጛይ፤ ጝሉዝመ ጅውነዙ ዊርተ ኻያቅ የነውዝ ኻቨረ ገቨይዝ ፅፃዝ ምላሰን ተረቊድ ሚቀቅ ቘልፍ (መንጋጋ ቆልፍ)፣ ጣዝጘ ፃየው ልኻን፣ ኻቭቀ አጛንድ፤ ዊስቭትዙ ዲምቅሽንዝ ጨቭጥዝመ ቂጥኝ ላዊስ ላዘይዝጎ ከረከረቊ ጛይ።
ቫይረስዝ ተረቁ፦ ዳቐዳቕሸነውዝ ከረከረቊ ግፈ፣ ኮቪድ 19፣ ኢቮላ፣ ኢንፍሎዌንዛ፣ ቀርቭርዙ ኪተትረ፣ ጉቑረው ግዝጝዙ ፅውዘ፣ ኩፍኝ፣ ቀርዝ ደግፍ፣ እፈርዙ ልምሸ፣ ቫይረስዙ ጎይተ ጛይ።
ፈንገስዝ ተረቁ ፅውዘን፦ ዊርተዙ ችግሰዝ ተረቁድ ኮሌራ፣ ጃርዲያ አሜባዝመ አጉለዙ አልተተ ኽፃ እንዝጘም መቈዙ አምልቀዝ ተረቊ ጛይ።
ክታ ወረደይል ኽይጠጘ ቲክንክነዝ አጋልዘቁ ከረከረተ ፅውዘን አውዛይ ጛይ?
እን አምረይዝ ጣይትንዝመ ፍጥሩ ኻደገን ቈሸቈሽትጝ መልቁ እፈሪል ሚዝል ፣ አቚ እኹረ ፅውዘን፣ አባ ሰንጋ (አንትራክስ) እንዝጘም ኻቭቀ ኽይጠጘዝ አጋልዝጝ ዊነቁ ከረከረተ ፅውዘን ጛይ፤ አነጚ አትርን ሰራሽነው ሰቪዝ አጉረውዝ ፈራቒንቀት ነንት ሰቲዝ እግዝግዘነው ቸልንኩኑን። ተረቲዝም እነየቁ ችግሰንጢዝ አጋልሽታየጘ ቃውሰ አስልሽት ፃቭሽት ኽዝቪዝ ልብሰነ ይውሽታጙ 18 ትኽነዙ ፓኬጀንድ ቲግቭሪል ግሪስጠጘድ ፃቭናጙ የጝ።
ጫረይጅቅ ፃየፃይሽትጝ ተረቁ ፅውዝጢስ እቀ ኽቭርድ ጝቕመት አወሽ ኻይጠ ጡሸኲ?
- ጛሉ ዊርተ ኻየነው፦ኒቭስ፣ፅቭቀ፣እርቁጣንዝመ ላዘድቅ ጊዝ ጨቨቅ እቓረነው፤ፅጓን ጋፅድ ግረቨዝ ግረቨዝ እቓረነው
- አምንሰተ አቕየው ዊርቨዙ አቑ ብልቁዝን ዝየነው
- ሚርምርሽየው ቑጥን ስየ ጂስን፣ፃቭ ብልቁዝን፣ አትክልተንዝመ ፍረ ምረንድ ዊርሽን እቓሰነውዝ ጂስን አሩሸነው።
- ሊን ጂስኑ ህዋሳተን ፍራየጘድ ቓዝቒስን እቑረነውዝ ኾነው በኒሳንድ ሊጘት ጥውሸውዝ ብርዘነው።
ማፅንፅንሸው ኹረ ኾነው ።
- ድድምድ ዋልጠ እርፍዝ ኲየንት እቁዙ ፃቭ ጭቑ ኒቭጠ ፃቨነው ዝመ ጝዝ እግርገም ቈሽተተ ኹረ ይወነውዝ ላው አምረ አሽ ኒቭሰነው።
- አዊንም አይንት ቅብረተ ኻቨረ ገቨድ ጥውሸውዝ ዊርሸነው(ድሰነው)፤ይዘው ኻቨረድ ቃጥለነው
- አርወ (Toilet) ፍነት እግርገ ዊትርቅም ናንድ ሰሙነዝ እቓረነው(ሰሙነ ብሽታን ፃብረዝ እቓረነው)
- ከየ ጒይጥ ላውዝ ላው ዊስንሸነው፤ አቕየውዜ ኮንዶም አሩሸነው።
- ትነርዝመ አምልቀ ፍረነ አቐቊ አቑ አቁለቁድ ቅብሰነውዝ ዊርሸነው
- ፅበነ ጝንጥድ ዊርየው አየር ፅብጠጘድ ፃቨነው
- ፅዊትኑዝጌ ጛጝን ጎየነው፣ ናንድ ደግምግምን እቓረነው፤ አቑ ዝመ ሰሙነ ችጝሻው ጊዚዝ ፅጓን 70% አልኮል አሩሸነው፣ ኪውም አነ ሰራሸነ ስፍረይል ዳቐዳቕነቁ ገባንድ(ስፍልድ) ጊዝጨቨቅ ዊርሸነው።
- አጡ ኹረ ኾነውዝ አካልዙ ፍልውልወ ፃቨነውዝ አጡ ዝሞ ችጘነው። ቲንፍሰነ አካላንድ ሺፍነነ (mask) አሩሸነው
ኪሮስ ወ/ተንሳይ
መዝየ 30/2017