ላው ስታዲየም ዓልም አቅቨዝመ አኽጉር አቅቨ ዋርደንጥድ አቭኑሰናንስ ካፍቱ ሳስ የው ሊኪየነድ እቻዘነው ጡሸኩ።
ሊኪየንም ማኽሊስም ኩኑቱ ዋርደንጥ አክንወናንስ ቸልሰው ባውዘዙ ሺከ፣ ተግድ ኻየው እጅር ሰራሸተ ፃቀ ወፃሸው ሺወ፣ ቪ.አይ.ፒ (VIP) ዝመ ቪቪ አይ ፒ (VVIP) የነትም ኪብርሸቁ አብንዝመ ስልጣን ጒይጥዝ ጎየንጥ፣ ዋርደጢዙ፣ ደጝጥዝመ ትኻዝቨጥዙ ሲረነ ክፍለን እንዝጘም ሚድየዙ ክፍል ፅብጠ ጡሸጘ ካፍ ፊሰው ሚዝረድ ቓሊሰኩ።
ኢትዮጵየትል ላውም ካፍቱ ሊኪየነድ እቻዘው ስታዲየም እጀው አቐነዊዝ ብሔሩ ጓነድ ኻግር ቢዘቱ ዋርደንጥድ አክንዋጙ ችጝሸኩ። ዋልያንድ ዲቈቊ ዊትቊ እምተኒዝ ዓልምትዊዝመ አፍሪከቱ ወንጨ ዊርሸነ ፃቨናንስ ኻግር ቢዘ ኻግሪዝጐ ሲድሽጝኩጙ።
እኒን ቈሽ ብሔሩ ጓነይዙ ፈኒል ጥቕዘ ጭሰነዊስ ከስጘ ኢትዮጵየት አጉረተ ጊንዝቭ ፊስራንስ ፃቫጙ የጝ። ነን ግነ እን ችግሰድ ቓቭዘው ጂጘ ተረው ሲንቱ አርፈ አሰነይዝ ወይሽተው አቐጘ ባሕርዳርቱ ዓልም አቅቨ ስታዲየም ደርግቭሸተ ሰቭ ፃጝዘተ አት ምስክር ሰውነት በኲር ስፖርት አስለ ክፍሊዝ ዊግትጝኩጙ።
ባሕር ዳርቱ ስታዲየም 2002 ዓ.ስ ኲንሸነው ኪርመው አቓንድ፤ኪርምሸው ሲዘትረ አምረይዝ እንቅ ኢትዮጵየቱ ዋርደንጥድ አቭኑስኩ።2015 ዓ.ስዝ ኪርም ግነ ካፍቱ ሊኪየንጥድ እቻዘናንስመ አግልግለይዝ ተሚሰተ አቐቊ ሲርይቁ እፍርታንድ ኲንሽጛጙ የጝ።
ባሕር ዳርቱ ዓልም አቅቨ ስታዲየም 52 ሽኽ ቓለጥድ አቭኑሰነውዙ ኻይል ፃየው የጝ። ጎየነ ዊንብረንድ ጋጥመነውዙ ሰቭ ሰራሽታጙ አቓንድ፤ 47 ሽኽዝ 500 ዊንብረን ነንትል አሽ ጋጥምሽጝኩጙ።
ጣቅ ኰሪዝም እዳቐቊ ሲዘ ሽኽዝ አኰላ ዊንብረን ጋጥመቁ አጘኲ። ጭቑረድ ሲሪንቀት (ቅውሪንቀት) ዊንብር ጋጥመነውዙ ሰቭ ሰራሽተነውድ ዊንብረንድ ደረጀድ ኻየቁ ብርትዝመ ቕዝቕዘድ ችበችብረነውዝ ቃዚጝ ጨቅሻቁ እንዝጘም ልየ ጓን እኳን ቃጥልሻቁ አቐነውድም አት ምስክር ሰውነት ዊግትጘኲ።
ፕሬዝዴንሺያልቱ (ቪቪ አይፒ) ክፍለን ጥቅለ 30 ዊንብረን ጣቅ ኰሪዝ ጋጥመቁ አቐነዊዝመ ጥይት ባቑዛው መስታቪት ሰራሽተኩ። ጝቕመቱ ካፍቴሪያ ዝመ ሬስቶራንትም ፃየው የጝ፤ ይሽታንድ ቪ.አይ.ፒ. ቈሽ 100 እቅ ፃየነው ቸለኩም ይሽትኩ።
ይና ኻግርስ ቃውሰተ አቐው ስታዲየሚዙ ልኰ ኳስዙ ሺወድ ፃቀ ሲርኩ፤ እሩዘነውዙ ሰቭም ፈረንሳይቱ ግሪጎሪ ድርጅት አክንወኩ። ስወዝ ምላሰን ዋርደ ቀቭሽታየጘም አቑድ ፅቃ ሴኮንድዝ ጥቅል ቢዘ ቅብሰው ቴክኖሎጂ ጋጥመነውድም ድቁሽትኩ።
አይነተ ስታዲየሚስ ከስጘ ተግድ ኻየቁ ሊጘ ዲዝጝዝጘነዙ ሺወንድ ላውድ ፃቀ ሲር ኻትሸው አቓንድ፤ ሊጘትረድ ቈሽ ጣቅ ኰሪዝ ሲረኩ ይሽትኩ። እንዳይ ዲዝጝዝጘነ ጭቑ አይንቀት ዋርደንጥድም አቭኑሰቁ አጘጘ ጋልፅሽትኩ።
ጝታ ላው ላው ሺወንድ ሻቘ ሽኽዝ 500 ዊንብረን ፃየቁ ጛይ፤ እቓረነዝመ ሲረነ ክፍለንም ፃየቁ ጛይ።
አይነተ ሺወድ ሸወጭዝ ሲዘ ግርቅ ዋርደንጥድ አቭኑሰነው ቸለው አቓንድ፤ እዳቀቊ ግርቂዝ ዋርደንጥድ ዲዝጝዝጘነ ሺወኒል ፃቭሽተኩ።እን ዲዝጝዝጘነ ሺወንድ ካፍቱ ጊምግመተ ጓነይዝ ሊጘትረዝመ ሻቘትረ ሺወ አቕጝ ሚዝግቭሽጝጠጘድ ፃቭኩ።
ለዊዝመ ፃግቪዝ ሊጘ ቴሌቪዥንዙ አጉረተ እስክሪነን ሲቅልሸቁ አጛንድ፤ ጝታ ፍራትድም 100 ካሬ ሜትር የጝ። ቻይናስም ጅቭሽጝ ኻግር አቒል ጥውጝኩጙ።
ኩኑቱ ዋርደንጥድ አክንወናንስ 20 ባውዘዙ ሺከን ቲክልሸቁ አጛንድ፤ ትንዝጘው ሺከዙ ቲነድም (Lux)1600 የጝ። እኒንም አልም አቅቨ ስታዲየመኒል ቲክልሸው ደረጀድ ኻየው የጝ። ተከተከውዝ ሊጘ ዲዝጝዝጘነ ሺወኒልም ሰውጠ ባውዘን ቲክልሸቁ አጘጘም ጋልፅሽትኩ።
ስታድየምድ ሲዘ ሲረነ ክፍለን ፃየው አቓንድ፤ ጋጥመ ጓነንድ ሲረነ ክፍለኒል ጥውጛንድም አነ ፍጛንድ ስረንታየጘ ፃቭሽት ሰራሽትኩ።
አዊንም አልሚስ ተረቁ ጭቅተ ዋርደንድ ትንዘቁ 120 ሚድየ ጉይጢዝ ክፍለን አስልሽጝኩጙ። ቪቪ አይፒ፣ ሚዲየዙ ሙየ ጉይጢዙ መኪነ ችብሰነ ደረጀድ ኻየው አስፋልትዝ ሰራሽተኩ። ስቴዲየምድ ልኰ ኳሲዝ ከስጘ 21 ስፖርተንድም አቭኑሰነው ቸለኩ።
ባሕር ዳርቱ ዓልም አቅቨ ስቴዲየም ንቅፀቁ ውሸብሊዝ ሰቭዙ አገነ ፋጥረው አቐጘ ጋልፅሽተው አቓንድ፤ ካፍቴሪያ፣ ሱቀን፣ ቲያትር፣ ኮንሰርት ዝመ ላጥም አግልግለን ይወዉ አቐጘ ጋልፅሽትኩ።
ጭቑረድ ሲሰናንስ ነንቱ አርየዙ ወየይዝ ሊጘ ቢሊዮን ቁርሽ አብዘው አቐነዊዝ፤ እንጎይስ ምጝግስትዝመ ላጥ ከቨተ ድርጅተኒል ከቨ (ርዳተ) አኽቭሻጙ አቐጘም ሰቭ ፃጝዘተድ ጋልፅጝኩጙ።
ኪሮስ ወ/ተንሳይ
መጋቪት 30/2017