ይና ጅውነይዝ ቲስመመቍድ ቺዝን ቲክልነ ጡሸኩ ይጛንድ አቭርገሌ ወረደዙ ፅበጥ ዊግትጙ

‎‎እጉርትቍ (ኽፅምትቍ) ግሪክትቍዝመ  ሮማቁድ  ዘፍ ቲክለነውዙ አጉረው ዲዝጝት ፃየቍ ዊንጘጘድ ድቍሽተኩ። ሮማውያንድ ኽፅምቱ ችግኝ ቲክለነውዙ ጥቨቭድ ጝታ መፃፋኒል ፃፈነውዝ ነን ፅበው ኹሪዝ እቑርጝኩጙ። ችግኝ ቲክለነ ቢጙ አወይ ፃርሸጘድ፣ ፍላኒዙ ስርድ አወሽን ሊሚደነው ጡሸጘድ፣ ቲክልሸቍ ችግኝድ ኮረይስም አነ ፊግየይጅቅ ፃይጘው ዚነይዝመ  ላጥም ችግኝ ሊጊሰነ መላንድ ሮማቁድ ነን ፅበው እገረ ኹሪዝ ከስጝኩጙ። ሮማቁድ ተክለንዝመ ፍረምረን ቲክለነውዙ ጥቨቭዝ አርቕሽተቍ ዊንጘጘድም ጝታ ድርሳናትድ ቓሊስጘኩ። እጉርቱ ትውፅውዘዝ ዲቍረይሸን ይና ኻግርም ግሪክስመ ሮማስ ፅጉየው አቕንትዝ ኻግር ቢቍለጥ ዘፍዝቍ ዚረድ ሊሚድን ዊንዘነውጅቅ ፃየፃይሽተው ሲጘ ፃይረይ ጚ።

‎‎ፍጥርዝ ችጝሸቍ እፅዋታኒስ ከስጘዝ  አጤ ምኒሊክ ጝታ ዚምነ መንግስቲዝ ባህር ዘፍዙ ዚረድ አውስትራሊየስ ነስሰነውዝ ቺተቺተቍ ኻግርሸንትቍ ጅውንጢል ቲክልሽጥጘ ፃቨነዊዙ ሲጘ ችግኝ ቲክልንጅቅ ፃየፃይስጠ ቸለው 1886 ዓ.ስዙ ሲጘ የጝ።  አጤ ምኒሊክ ዘፍዙ ችግኝድ ፍልዘነውዝ ቲክልሸነውዙ እድሚል ችጛንድ ኽዝቭድ ችግኝድ ፊሳጙ ቲክልጠጘድ ኻስቨነውዝ  “ባህር ዛፍ ቲክልሸው ቺዝጚዙ ግቭርድ ሳቑትኩን ” የው ቒየ ፊስጝ፣ ኽዝቭድም ሸማሽ ቲክላጙ ዊነጘድም  ዻውሎስ ኞኞ አጤ ምኒሊክ የው ጝታ መፃፊል ሲፍርዝጝኩጙ።

‎‎ይና ኻግር ኢትዮጵየ ችግኝ ፍልዝን ቲክለነውዙ ሲጘ ጋብዝ 19ትረ አድለ ዚምኒዙ በተነይጅቅ ፃየፃይሽተው አቕሽም ቺተቺተቍ ፍጥርዝ ቢቍለቍ ዘፋንድ ሊሚስን ዊንዘነውዙ ዲዝጝትድ ግነ ንቕፀቍ ላ እምታንድ ከረው የጝ። ምከንጣኒል፣ ኽፅምትቍ መስጊዳኒዝመ ንጉሳነ ኻፅርድ  ሺፍንጝ ችጝሸቍ ዘፋንድ እንዝ ቓሊሰነ ጛይ።

‎‎ኢትዮጵየቱ ዝቨይስ 40 ላይስ አቐው ዝቨድ ደንዝ ሺፍንሸው  ዊነጘዝመ  ቺተቺተቍ ችግሰጥ ምላሰንዝ  3 ላይዝጎ ጊመጘድ ሚዝርጥ ቓሊስጘኩ። ኢትዮጵየቱ ሚሊኒየምድ ቅሸነውድ ቲክን 2000 ዓ.ስ አክኑሸው ቅስቀሰዙ ሰቪዝ ዝምረዝ ችግኝ ቲክለነው ኪርምሸት እንጎ 3 ላይስ 15 ላይዝጎ ኪፍ ሸነው ቸልሽኩ።

‎‎እኔን ቲግቭርድ አትር ቃፅል ነንቱ ሰቲዝም ኢትዮጵየ አምረ ጨቨቅ አልቛዘ ደፈ የው ፕሮግራም አስልድር ብጭቕ ቢሊዮንዝ እጊተቍ ችግኝ ቺተቺተቍ ደንዝ ይሽትጝ ጊግቭሸቍ ስፍልል ቲክልዳጙ ችጝሸች። ዊገድ ግነ ላውላው ስፍሊል ቲክልሸቍ ችግኝድ ተክልሽጛንድ ጚ ሊግዝጛንድ ቓልሽተለም። እንም አጠ ቸለውድ አውየን ፍልድ አውየን ስፍረይል የጝ ቲስመመውድ የውድ ፅንኸል ሲሪሸው አየው አቐነውድ የጝ።

‎‎ወይ ኽምረ ብሄረ እቅ ጭሰጭሰን አቭርገሌ ወረደ ፅበቍ ጒዝጝ ጨጥዝመ ሙየ ጒጥድም እኔንት የጝ ደድስጘውድ።

‎‎አት ሀፍቱ ጎነጠ አቭርገሌ ወረደ 01 ቀቨሌዙ ፅበተ ነይጘው ቓለይዝ፣ አምረ ጨቨቅ ቲክልሸቍ ችግኚስ ሚም ይሽተው ዘፍድ ጭቑ ፃድቃጙ አቐጘዝመ ጘጝም አቕሽ ኒየረ አቑ ኻትመይዝመ ምከንጣኒል ጭቑ ቲክልሸው አቐነውድ ጋልፅጝ ” ይና ጅውነድ ጝቕም ቢቍልዘቍ ቃነ ማንድ እንሰሲስም አነ እጅርዙ ዳቐዳቕኒስ ናፀ ፃቨነው ቸልሻን ጛይ ጛይ ይና ጅውነይል ሊግዝጥጘ ቸለቍድ ” የነውዝ ዊግትጝኩጙ።

‎‎ላየ ቓለ ነየተድ አት ገ/ ሚካኤል አናይ ጝታ ጋቢዝ ጝታ ቀቨሊል ፅበው ቢሩ ይሽተው ጊግቭሸው ቅብረድ ጡሸውዝ ሊሚደነው ቸልሸውዜ ላየ ጅውነይስ ነስን አርቕሽትየው ችጝኝ ነስን ቲክለነው በንዛው አቐነውድ ጋልፅጝ” ይና ኻትመይጅቅ ቲስመመው ይሽተው ዘፍድም አቕሽ ፃመዝ ጚ ላየ አርወዝ ግርያው አቓንስቅ ይና ፍጥርዝ ችጝነቍ እፅዋታንድ ታኽንኽንን ሊጊሰነው ቸልነውዜ ጝታ ፃመድ ፈወነ፣ ጝታ ፍርድ ኹን እፍተነ በንዘው ኮሪዝ ቈሽ ሊነ እርቭነ ፃቭን አሩሽነቍ አጛንስቅ ጛት ታኽንኽነ ጡሸኩ” ይጝኩጙ።

‎‎ሊሚሽጝ ዊነቍ ቅብረጥድ ጣይትኒዝ ምላሰንዝ ሸርጝ ዊነው ቃነማነድቅ ድዘነውድ ዊግተቍድ አት ገ/ ሚካኤል “ነንም አቕሽ ይና ጅውነድ ሊሚደነው ቸልነውዜ ዊነው ቃነ ማነድ በውዝ ዋጥረው አቓንስቅ እንቅ ሊሚድነ ጡሸኩ” የቍ አጛንድ ቺተዝም ቈዘነዝመ ክሰለዝ ይጛጙ ድርድ ማፅረቍ ላውላው እቅድ ጝታ ቲግቭሪስ ቋጥቭሽጥጘ ጡሸጘድም ኻስቭዝጝኩጙ።

‎‎አት አለምነው ስጦታው አቭርገሌ ወረደ 01 ቀቨሊዙ አርሽነይ ፅፈሽ ጝኒዙ ዲቈተ ይጘጘድ  ወረደድ ቈለዝመ አጉረው ብርት ፃየው አቓንስቅ እኔን ብርትድ ማኽተነው ቸልሸውድ ዘፋን ቲክልን ሊጊሰነውዝ አቐነውድ ጋልፅጝ “ነን ኻትርሸውዝ ፃድቅ ልውጠ ቓሊሳጙ ፅበው ችግኝድ ሚም ይሽተው ችግኝድ የጝ፤ ጘጝም ኻትመይዝመ ኻትመይዝ ጅሉዘ ፅበቍ ምከንጣኒስ ቢዘ ቲክለነው ቸሊነቅም ” የቍ አጛንድ ወረደይዝጘድ ንቕፀው ፍጥሩ እፅዋት ፅበነው አቓንስቅ ዲዝጝጝ ቃነ ማነድ ታኽንኽነነዊል ትኩርት ይውጝ ሰራሽጛጙ አቐነውድም ጋልፅጝኩጙ።

‎‎ተረው አልቛዘ ደፈዙ ሰቪዝ አቐቍ 30 ሽኽ ፍላን ፍልዝጛጙ ችጝሽጘጘድ ጋልፀቍ ሙየ ጉሬድ ” ቲክልሽጘው ስፍረድም GPSዝ ልክን ቺዘነውዝ ቃውሰ አስልሽት ፃቭንኩኑን” የቍ አጛንድ ነንም አቕሽ ጅውነይጅቅ ዲዝጝሸቍዝመ ፍጥርዝ ችጝሸቍ ችግኚዝ ትኩርት ይወቍ አቐነውድም የጝ ጋልፅጘውድ።

‎‎አት አስማማው ደባሽ አቭርገሌ ወረደ አርሽነይ ፅፈሽ ጝኒዝ ፍጥሩ ፃጀ ጓነ ቃወተ ይጘጘድ ወረደይዝጘድ 17 ቀቨሊጢል 50 ቅብረጥ ፅብጘጘድ ጋልፅጝ 2016/17ዝ 11ሽኽዝ 1 ላዝ 17 ችግኝ ቲክልጘጘዝመ፣ ቲክልሸቊስም “9 ሽኽዝ 4 ላዝ 17 ችግኝ ፃድቅዘነው ቸልንኩኑን” የቍ አጛንድ፣ ጥቅለ ፃድቅንዙ ምፅነድ ቓልሽታንድም ቺዘው አቐነውድ የጝ ጋልፅጘውድ።

‎‎ተረው 2017/18 ጊቭርትዙ ዚምኒዝም 4ላ ሽኽ ችግኝ ቲክለናንስ ኻለይ ፃይሽትኩ የቍድ አት አስማማው፣ “እንዳት ቲክለናንስ ቸልሰው 23 ነቍጠ 75 ሄክታር ዝቨ ቺዘነውዝ አስልሽንኩኑን” የቍ አጛንድ ኺጠዝም ጅውነድ ዲዝጘቍ እፅዋታኒል ትኩርት ፃቭን ሰራሸነው በንዘው አቐጘድም የጝ ጋልፅጘውድ።

‎‎ዝቨ ቢቁልዛይረው እጅረይም ዝቨይጅቅ ቲስመመቍ እፅዋታንድ ቺዘነውዝ አውየን አውል ቲክልሻንድ ቺዝጡ የነውዝ ፅንኸል ሲሪሽን ሰራሸነው ግነ አምኮርት አቐነውድ የጝ ቓለ ነየጥድ ማኽርጘውድ።

ንጉሱ ማሩ

መዝየ 15/2017

- Advertisement -spot_img
- Advertisement -spot_img

Latest article

AMECO Himitgna