ኢድ አል አድሃ አራፋ

 አልምት ጅሉዘይል እስልምነዙ ኻይማኖት ቲክነጢዝ እብለውትዝ ኪብርሸቁ በለኒስ ላውድኢድ አል አድሃ (አረፋ) የጝ። በልድ እዝወነ ዊንም መስዋዕትነይዙ በልም ይሽተነውዝ አርቕሽተኩ።

አረፋቱ ግርየ  ሂጅራቱ እግዝግዝኒስ አሰነይዙ አርፈ አቐው ዙል ሂጃህ ጥወዉ ፃይጨትረ ግርየይስ ግርየኲ። እልቲስ ሃጂቱ ጉዥተጥ አራፋት ቲረይዝጎ ፈነውዝ ቺተቺተቁ ኻይማኖቱ ስረተንድ ፋፅምጘኲ። ሃጂዝ  ሳኡዲትጎ ፊረቁ ሙስሊመን ኢድ አል አድሃቱ በልድ ላው ግርየ ቃውስ ይጝ አራፋቱ ቲረይዝጎ ፍጘኲ።

አራፋቱ ቲረይል ፈነው ሃጂ ጉዥተጢስ ቺተው እክሰ ፃየው የጝ።ሃጂቱ ጉዥተጥ ስቑርትዝመ አኑ እንዝጘምመስዕዋይትነይ ቓሊሰነ አቐው ግርየይዝ ቲረድ ፈነው አሏህጅቅ አልተነውዙ አገነ ነየኩ ይጝ አምንጘኲ።

አሏህቱ ቀሰው እጅር   ነብዩ ኢብራሂም 120 እምት ማኽንድንዝ እግርገ አላህቱ ፈቃዲዝ ጊር ኹር እኹርጝ ጠጘድ ፊቅዱ።  ጝታኹር ኢስማኤል ጝታይርስ አዚተተ ዊነጘም ድቁሽተኩ።

ነብዩ ኢብራሂም ጝታ እምጥጘይስ ጛምርስ ጝታ እምንቲዙ ፀናቕንድ ፊትነው ኰር ፋጥርሹ። ላጝጠ እምቱ ላው ጝታ ኹርት መስዕዋትነይ ፃቭጛንስ አላህስ አዚትጙ። ጝታኹርት ቀንትድ ጨንቂስሽም  አዝንድ እደረቱ አቓንስቅ ፋፅመናንስ መካቲስ አራፋቱ (አራራት) ቲረይዝጎ ፍጙ።

ነብዩ ኢብራሂም ጝታኹርት መስዋዕት አልስጥጘ አስልሽጛንድ ኢስማኤልት ፊንተይዝ አቐው ቢገዙ ምፁነ ጊሙ። በልድም ኢድ አል አድሃ (አረፋ) ይሽታጙ አምረ ጨቨቅ ኪብርሸኩ።

አረፋቱ ኪብርዝን ላዘ ሲጙ ጋልፅሽተነ ፃየው አቐጘም ቁራን ቓሊሰኩ።አደምስመ ሃዋስ አላህቱ አዝንድ ጒድልዘነዊስጎው ገነትስ ዝቨቱ አልምትል ጀጊትጝ ቺተቺትጝ ፅብጘት እግርገ ቃውሰው ጊዝዝ ዲምቅሽጘውድ “አርዱል አረፋ” ይሽት ጭጝሸው አራፋቱ አበይል አቐነዊዝ “ረፍኪኒ፣ አረፍቲኒ”ይሽተይሽተነውድ ኻስቨነም (ዚክረነም) የጝ።

መካቲሰ ምስራቅትጎ 20 ኪሎሜትር እክልድ ችጝሸው ቅዱስ ቲረድ ቓለነውዝመ ኻይማኖቱ ስረተንድ  እድጝል ፋፅመነው ጥውሸጘም እስልምነ ኻይማኖቱ ክንድጝድ አዘኲ።

ኰረ ጥውትዊል አሽም ቅዱስ ቁርአን አንቭቭጛጙ፣አላህት ሚዜንዘነውዝመ ምኽርትዙ ናንድ ዘርጋቓንስ ጨወነውዝ ዊንተ ፃቭጘኲ።

ናሚራቱ መስጂድ ኢማም አራፋቱ ግርየዝ ማጥን ይውጘው ኻይማኖቱ ክንድጘድ እስልምነዝ ኽየው ስፍረ ፃየው የጝ።  ሃጂ ጉዥተጥድ ኰረ ጥውረት እግርገም መካቱ ጅውነይል ችጝሸውዝመ ንቕፀቁ እቅ አቭኑሰነው  ቸለው ሙዝዳሊፋህ ትጎ ፊረነውዝ እዳቐው ኻይማኖቱ ስረተንድ አክንውጝ ፈውጘኲ።

ሙስሊመን መስዕዋትነይዙ በልድ እዝወነውዝ፣ላብጠ ፀሎት ፃቨነውዝመ አላህስ ምኽርት ችጘው ቀሰቊ ቲግቭረን አክንወነውዝ ዲቁስጘኲ።

አል አረቢያ ዚግቫንትጘድ አቐውዜ ንጭቱ   ኢድ አል አድሃ በል ግንቭት  29 ግርየ 2017 ዓ.ስ  ኪብርሸኩ ይሽት ኻስቭሸጘ ፊሰው ሚዝረድ ቓሊሰኩ፡፡

እምንትድ ቲክነቊዝ ቅዱስ ስፍረዝጘ ቓልሽትረይ መካ ቈሽ በልድ እብለውትዝ ኪብርዘነ አራንድ፤እንቅ አልምት አድለይል ችጝሸቁ በልድ አድልሸናንስ ስፍረይዝጎ ጉዥትጘኩ።

እስልምነዙ ዕምንት ዝቨይል ጝሩሔዝ ሊን መካችጝሸውአላህት ሚዜንዘናንስ ደምዝ ፃየጘ ጋልፅሽተው አቓንድ፤  ሳውዲ አረቢያም አምረ ጨቨቅ ሃጂ ጉዥተጥ እንቅ አልምትል ችጝሸቁ እስለሚስ ለውርድንዙ አገነ ይወች።

እን ሃጂቱ ጉዥትኒስም ሲርየ መካ ትጎ ፊረቊ እስልምነ ቲክነጥ ንቕፀነዊዝ ምላሰን ደድሸነውዝመ ዝላዝ ክረቊ ዜገኒዙ እግዘድም ቀለውዝ ቓልሽተው አየውም።

ሊጘ እምትዝ በውግ የነትም 2015(2023)  ሃጅቱ  በሊል 1 ነቁጠ 8ሚሊዮን ዜገን ሳውዲትጎ ጉዥተቊ አጛንድ፤ብርትዝመ ትክቨትክቭሸነውዝ ምላሰን 230 አምነጥ እቅዝ ንየ ጝታ ሩሔድ ዲቈጘ እንዝጘም 2016/2024 ቈሽ ብርትድ 50 ሴልሼስ ዲግሪ አቐነዊዝም 1 ሽኽዝ 300 ክርጘጘም ትኽነ ኻይን ሚኒስትር  ፋህድ አል-ጃላጄል ፊስጘው ጋልፀነድ አርቕሽተው የጝ።

ቀድሽተቊ ኻረን(ጥመን) እስልምነዝ ኪብረቊ ጛይ። አሏህ ጝ በሪል ኽየው ኽዝን ፃየው አቓንድ ላው ላው ኻረንድ ወየ ፃቭኩ። እን ኻረኒዝም ፃቭሽተቁ ዱዓንድ ለምረው አቐጘም ዊግትኩ። እን ኩነንጥድ ጝበሪዝ ንቕፀዝ ሲግድጛንስ፣ጸሎት ፃቭጛንስመ  ስቑርት ዋቕርጛንስ አገነ ይውኲ።

ኪሮስ ወ/ተንሳይ ግንቭት 30/2017

- Advertisement -spot_img
- Advertisement -spot_img

Latest article

AMECO Himitgna