አሚኮ ክልሊዙ ዲግዝመ ትውጽውጸዝ ጻቨው ልቕረድ እንቅ ልብት ከቭጠ ጡሸኲ!

ክልሊዙ ኻሰቭዙ ማዕከል አቐናንስ በኲር ጋዜጠዝ ማጥን እኹርሹ። ጋዜጠዝ ኪርመው ክልሊዙ ኽዝቪዝ አግልግለድ ኰርዝ ኰር ሊጊስኲ። ሬድዮ፣ ቴሌቭዥን ዝመ ዲጂታል ሚድየ ኲነነውዝ ፍልፍለ አቐነዊስ ዲቍ ዊግሽንዙ አርወዝመ አውር አቕኲ። ነን  አሚኮ 30 እምቱ ችብረ የጝ።

እን ጝፍራቲዝ ኽምጣጘ ቈጝቈድ ቈሽ 12 ቈጝቍጥዝ አግልግለድ ይወነውዝ ኢትዮጵየትል ትኒተቍ ብጭቕዙ ዲምቅሸንጢዝ ችጝሽተተዝመ ማርጽሽተተ አቐናንስ ሠራሻጙ የጝ።

ኽምጣጘ ቈጝቈዝም ኽምጠ ዊከ ጋዜጠ፣ ሬድዮ፣ ቴሌቭዥንዝመ ዲጂታል ሚድየዝ ዊግሽንድ ጽፈሽዝጎ፣ ጽፈሽድም ሚድየዙ ቈንቈይዝጎ ከሰከስኲ።

አሚኮ 30 ምቱ ጝጻጝቲዝ ኽዝቪዙ ጊቭርዘትነይ ንየስ ያንስ ሠራሸንጥድ ፈራዝኲ፤ ሚኲርሽንጥድም ለውርስኲ። ክልሊዙ ባኽልድ፣ ዲዝጝትድ፣ ቅርሰንድ፣ አርቐ አርቕሽታንስም ሚረ ብዝኲ። እንዝም አርቕሽትየቍድ ቓልሽትጛንስ፣ አርቕሽተቍድም ጒልምድጛንስ አገነ ፋጥርኲ። እን አገነድ  ቱሪስተን ዊትረነውዝ፣ ገቨድም ሊጊሰነውዝ ኢኮኖሚል ቀሰው አገነ ዋርድኲ።

አሚኮ ክልሊዙ ኽዝቭድ ፖለቲከዝ ነቃቐው፣ ሚዝረዝ ዊገዊግሸው አቓንስ እሴትዝ ጨቅሸውድ ጭቅ ያንስ ጻቨነውዝ ዲሞክራሲዙ ዲዝጝዝጘ ዊናንስ ቸልሰኲ።

ኽዝቭዝመ ምጝግሥት አልትልትጝ ሠራሽጛንስ ኻትመዙ መድረክ የነው አጽቨም ፈጣቐነውዝ በውዝ በው ጝታ ችግሰድ አልስጛንስ ላብጠም እክሰ ችጛንስ ጻቨነውዙ ዲዝጝት ፋጥርኲ።

አሚኮ ክንድጝዝ፣ ትኽነ ዚርፊዝ ብጭቕ ሳዝመ ንየዝ የቍ ገባንድ እሩድጛንስ ምሽኹት አቕኲ። ቃውሰ ሰባን ኻሊሽጝ ሠራሽትጛንስ፣ ፋጽምጽመድ ቀሰው አቓንስ፣ ተክዘ አቐቍድም ላጢዝ ክንሸነ አቕጛንስ ልቕርድኲ።

ኮርፖሬሽንድ አዊስቅም ወርየውዝ ኽዝቪዝ ችብረው አቐነውድ ክልልድ ቺተቺተቍ ስነ እዘንዙ፣ አካልዙዝመ ጭቅተዙ ጣይትኒል ጥወው ጨቨቅ ኽዝቭድ ጝወንት ኻያንስ በዊል አሽ፣ ጣይትንል አሽ ፊርን ዚግቨነውዝ ጝወይትነይድ ደድስኲ።

አቒቱ ኽምዘ ፋጥርሸቍ ጣቅ ምተኒዝም ድርል ጥወቍ እቅ ዲጊዝጎ ዋጥርጛንስ፣ ኪርምሸው አቒቱ ጣይትንድ ኽዝቪዝ አርዋው አቐጘ ሲለቲንቀ ድቍኲ። እን አቒቱ ኽምዘድ ኽዝቪዙ ፍልውልውን ሠራሸነውዙ ሚቭትድ ጊግቨው፣ እጅርነይዙ ሚቭት ማጥለው፣ ቓፅጚዝመ ማጥለጢዝ ሚቸው ፣ ኽዝቭድ ጕየው ዋቕረይዝመ እክሰድ ዳቅሳው አቐጘ ደግምግመዝ ዚግቭኲ። እንዝም ክልሊል አንጻሩ ዲግ ተራንስ ጝችጘርድ ፍኲ።

 

እን ጝሰቪዝ እድወ ብላ ክልሊዙ ምኽር ጝንድ አርቕትዙ ቘደ ይዋንድ ቃውስ የው ጥቅለተ ሚነስትር ዐብይ አህመድም “አሚኮ ቸለኲ” የነውዝ ቈድጝ ዊንጙ። እግረ እኔንትቅ ጻቫጙ ችጝሸው ኮርፖሬሽንድ ጻቨው ልቕረድ ልብትን ከቨነው ጡሸኲ።

 

አሚኮት ልብትን ከቨነው ክልሊዙ ተረዉ 25 እምቱ ስትራቴጂክ ኻለይድ እሩዳንስ ጻቨነው አቐነውድ አስክዘነው ጡሸኲ። አሚኮት ልብተነው የውም ከቨነው ጝታወንት ከቨነውዝመ ጝታ ዓምርድ ጭቅ ያንስ ጻቨነው አቐነውድ አርቐነው ተሚሰኲ።

አሚኮት ከቭሰነው የነት ብሔረ እቅ ጭሰጭሰንድ፣ ክ­­ልልድ እኒዝጘም ኻግሩ ትውፅውፀል እኩሰ ፃቨነው አቐነውድ ልብተነውዝ ተሚሰው ሚዝረድ ኮሪዝ ይወነው ላው አይነተ ገቭ አጠ ጥውሸኩ፡፡ ምላሰንድም ሚድየዝ ሚዝረ ይወነው አውማው እቀ ኽቭርዙ ሚብትዝመ ግዴተ አቕሽም ቺተዝም ቈሽ ምጝግስትዙ ዲቁትነይ ፅይን ሚዝረ ጊግቨነው ኽግዝ ዋቕርሰው አቐነውድ ልብተነውዝ አሚኮስ ሚዝረ ይወነው እቀ ኽቭሪዝ ሚዝረ ይወነው አቐነዊዝ ኰርድ ኻየው ሚዝረ ይወነውዙ ዲዝጝትድ ሊጊሰነውዝ እኩሰ ፃቭነ፡፡

ግርማ ተጫነ

ንኻሽ 15/2017

- Advertisement -spot_img
- Advertisement -spot_img

Latest article

AMECO Himitgna