ኢንዱስትሪዝ ሲሪሸዉ ኢኮኖሚ ፋጥረናንስ ልቅርድረይ ኢትዮጵየ ኮሪዙ ኢኮኖሚዉ ጝር ሲረድ አርሽነይ የጝ። አቐነዊዝም አርሽነይድ ተሚተዉ ሚልክዝ ኢኮኖሚድ መዉር አዉግረዉ ተጊል ችጛንስም እክሰቁ ቲግቭረን አክንዉሽጛጙ ችጝሽጘኩ። እንዝም ጎዉ ኻግርሸንቱ አርሽነይዙ ጊቭርትድ ምጽነዝም አነ አይንትዝ ሊግዛጙ ችጝሸኩ።
አነጚ ኢትዮጵየቱ አርሽነይድ ነንም ባኽሉ ጊቭርዘትነይ መለይስ እድቑጠም ሊቅሽየዉ አቐነዉዝ አይነተዝም ጊቭርትዙ አኽቭንዝመ ጝኮርድ ችጘዉ ኽወዙ በክንትድ ጒዝ ጨተይስ ጭቑ አይጝቀስ ኻግርዙ ኢኮኖሚዝም ጥቕዘ ጭሰነዉድ ዳቕየዉም። ይንም ንጭቱ ይና ጽፈሺዝ ችጘቁ አርድ ከቨከቭሽትን አኽቨነዉ ቲግቭርድ ዉር ተከዉ አቐጘን አንቭቭስነኩን።
ኮርድ ኽወዙ ታኽንኽነ ፍራትዝ አክንዉሸዉ የጝ።አዊስም ኮሪስ ቺተዉዝ ሲዙርን እግልድ፤ አትርንድ ሊቁስን ቺዘዉ ጊቭርትዝ አትረነ ኮር የጝ። ጒዝ ጨተድ ቺዘዉ ጊቭርት ችጘናንስ እቻቐዉ ኮርድ ጝታ ቺዝጚል ዲቑስጘዉ ኮር የጝ።
ጒዝጝ ጨጥድ ሰባንድ ለወንትዝ ሰራሸነዉ ባኽልቁ ጅመኒዝመ አስጘዝ ጅግነድ ወረወርዘነዉ ፣ሲዞረድ ቈሽ ዊቅሽተዉ ኮር የጝ።
“ሽልም ጻምርኩ ክቪድ እቻዝ ኻቭዝጠ
ሚስኩርም ተራንድ አትረጝ ሽዉረድ ኾስጠ”
“ሚስኩርም ተራንድ ጥቅምት ተራንድ
ግርቨቭሽ ቓል ኻቭዞድ ስጙርሽ ግርቪል አሽ”
ይጛንድ አጝኮረ ጒዝ ጨተድ ወረወርሽተኩ፤ ጝጝንድ ቻቐዉ አቐነዉድም ድቁሽተኩ።
እንኮሪዝ ጝኮርድ በክንዘዉ፣ ጝችዝጝድ ታኽንኽንየዉ ጝጊቭርትድ አርየል አልሰነዉድ ዳቕ ጝጝነቁድ ኾሰነዉ ቸልየዉ ሲዞረ ጒዝ ጨተድ ቈሽ
“ኻምል ንኻሽ ተራን አትር ጒዛዉ እጅር፣
ሚስኩርም ተራንድ ጋብራዉድ ከስ ቓለኩ፣
ግዝቅ አውም ይጭር”
የቁ ስነ ቃሉ አሥጘኒዝ ጉይሽተኩ።
እንትየቁ ስነ ቃለን አስጘን ጭቅተ ጒደነዝ ጋልፀቅ ይጝሽም ጅሉዘዝ ጝታ ጋቢል ጽበዉድ “አትር ጒዝ፣ አርም፣ ዃትኹትር ክድኽትድቲስ ሊቅሽ” ይጛጙ የጝነ ሲዞረ ጒዝ ጨተድ ዛሽታየጘ ጝጝነቁድም ጡዉሸዉዝ ቃዋንስ አትረዉ ጒዝ ጨተድ ንቕጽጠ ማጥን ጻቭሰኩ።
ጒዝጝ ጨጥድ ጝታ ሰቢዝ ማኽል ማልሸቁ ቃልዝቁ አስጘጥድ ወረወርዝጘዉድ ዛን ጭቑ አየዉም እክሰ ሚሪሰጥ ኻሠቫን ዲዝጝትዝመ ሚኩረንጥድ ቈሽ ሚዝረም ላዉጥዉጥሽጘዉ ክንደነዙ ጒደነ የጝ። ይነ አቅልድ ጛለስ ኾነዉ፣ ጛለስ ሰራሸነዉ ክንስየቁ አቐነዊዝም ላብጠ ሰራሸነዉ እጅር ኹሪዝ ጭሩ ጻቨነዉ ካዉረስ እምጥጘ ወይሰዉ አቐነዉድም ክንስጝኩጙ።
እደሴ ጭሩ ጻቨነዉ ኽጽምቲሥ ኪርም ይና አቅልድ ጻይጝ ተርጘዉ ላብጠነይድ ቓሊሰዉ ሰቭ የጝ። ኽዝኒዝም አነ እምጥጘዝ ጛስ ጛይቱ ገረዱ እጽቁጽቈንድ አትርዘዉ የጝ። ይነ አቅሊዝቁ ጭሩነይዝቁ ጋልጽሽተነ አቐቑ ሰባኒስም ኹራረዙ ሰቭድ ላዉድ የጝ። ኹራረ የነት ላዉ ጅውነይዝቁ እቀ ኽቭርድ አቨርድጝ አቅም እጀዉ እጅሪዝ ከቭሰነዉ፣ ጝን ተሠነዉ፣ ጒዘነዉ፣ አርመነዉ፣ ቃዉስ ችጘዉ አረድ በክናየጘድ አይረነዉዝመ ጊዝ ይዉጥጘ ቸላቁ ችግሰንጥድ አብርድንዝ እክሰነዉ ቀሰዉ ጻቨነዉዙ ስረት የጝ።
ወይ ኽምረ ብሄረ እቅ ጭሰጭሰን ዝቋለ ወረደ 01 ቀበሊዙ ጽበተ ጝታ ኻሠቭድ ስልክዝ ቢንሰቁ ጒዝጨተ አበባዉ ወልዳት ነንት ኮሪዝ ጫረ ጥወነዊስ በዉግ ጝታ ቺዝጝድ ደግምግምጝ ጒዘነዉዝመ ዛረ ቅብስጝ አጡ አቕንትዝ አስልጝ ፊዝጘዉ ቺዝጚል አጡ አቐዉ ጊቭርት ችጘናንሥ ሚስምርዝ ፊዘነዊስ ኪርም አርመድ አርምጛጙ ጫቕጝ ጝታ ጅዉነድ ቈለ አቐነዊዝ ቃዚጝ ችጘቑ ኽወጥድ ቺተ ቺተዉ ኾይረዝመ ጝኮርድ ኻይየዉ ስወዝ ቈይሻየጘን ኹራረዝመ ልቭነዝ ሰራሸናንስ አስልሸቁ አቐነዉድ ዊግትጘኩ። “ኹራረዙ ሰቭ እቀኽቭሪዙ ላወንትነይድ አትርዘዉ ጊዝዝመ ጊንዝብ እኒዝጘም ግርብ በክናየጘድ ከብሰዉ አቅም እጀቁዝመ ቈይሸቁ እቅድ ከቭሰነዉዙ ሰቭ ጥቅለዝም አቭርድንድ ቃሊሰዉ የጝ።” ንጭቱ ጫረይዝ አርመዙ ሰቭድ ኹራረዝ አርምጛጙ አይርጝ ጣብጥጙዊል አሽም ላብጠ ሰራሸቁ አቐነዉድም ዊግትጝኩጙ።
ላየ ስልክዝ ዊግስነቁ ጒዝ ጨተ ወለለ ወ/ስላሥ 2017/18ጊቭርትዙ ዚምኒዝ 2 ሄክታር አጡ ጝታ ቺዝጝድ ቺተቺተቁ ኽወኒዝ ሺፍነናንስ ቃዉስጝ ደግምግመዝ ጒዘነዉዝ ጝታ ዝቨድ ዚረዝ ሺፍነነዉ ቸልጝኩጙ። ጒዝ ጨተድ ይጛን ትጘም ጊቭርትድ ሊግስጥጘ ቸለቁ ጥወራንድ ቃዉስጝ ጅቨነዉዝ አስልሽት ጻቭጝኩጙ። ተክዘዝም ማርጽሽተዉ ዚረ እጅር ሰራሸተ ብጥዙ እፍርዘነዝመ ላጥ ጥወራንድቅ ቃዉስጝ ጝታናኒል ድዉስጝኩጙ። ጥቅለ ጫረይዝም መይለ እንቁ ደዉሰዝመ ጣቭ ፊዝጝኩጙ። ፊተቁ ኽወንድ ታኽንኽነነው የቊድ ጒዝጨተድ ጋቢዝ ጋብ ተረዊዝ ሚንወዝ ፊዘናንስ አስልሽት ጻቭጛጙ ችጝሽጘንትጘ
ጅውነይል ኹራረ ጨወዉ እጅሪል ዳቐነዉ ኒዉር አቐነዉድ ጒዝ ጨተ ወለለ ወ/ ስላሴ ጉየነዉዝ “ጫረድ ጥወት ኪርም ጒዘነዉዝመ አርመዙ ሰቭድ ኹራረዝ ልብነዝ ሰራሸነዉዝ ቀሰዉ ጊቭርት ችጘናንሥ ኮርድ ኻይን ሰራሽናጙ ግርብ እጀቁዙ ኽወድ አኽቭሽንቀ ቺተቺተዉ ኻደገዝ አጋልሽታየጘን እጉርም ሰራሽናጙ ተርነዉ ይነ ባኽል የጝ ነንም ሰራሽናጙ ቸጝሽነኩን” ይጛንድ ዊግትጝኩጙ።
ዝቛለ ወረደ 01 ቀቨሊዙ አርሽነይ ጽ/ጝንዙ ዲቈተ አት ገሸይ ቸኮለ ቀቨሊዝጘ 478 ሄክታር ዝቨ አጡድ ኽወዝ ሺፍነናንስ ኻሊሽት ኻሊሸዉድ አቻቐዉዝ እቻቐዉ ኽወዝ ሺፍንሸዉ አቓንድ ጊቭርትነይድ ሊጊሰናንስ አርመዙ ሰቭል ቲኩርት ጻቭሽት ሰራሽታጙ ዊነጘዝመ ችጘቁ ኽወጥድ ኮሪዝ አኽቨናንስ “ላዉ አኮቱ ተገተግሽትኒስ ቈሸዝ ኹራረዝመ ልቭነ አሩሽጝ ጝኮርድ ኻይየዉ ስወ ጽብጠ ቸለኩ የነዉዝ ቃዉስን ጣንቅቅሰነዉዝ ጊቭርትድ አኽቨነዉዙ ጻጝትድ ፈራቐዉ ሊቨሊቭን ጻቭሽታጙ ችጝሸኩ” ስወድ ዊቱ እግርተነዊዝ ዘስክረነዉ ቓልሽተነዉድ ጝወንቱ ጥቕዘ ጭሰዉ አቐነዉድ የጝ ሙየ ጉሬድ ጋልጽጘዉድ፤ ጒዝጨተድ አምረድቅ ልቕርደዉ ጊቭርትድ ጥንቅቀዙ ግትንዝ ምላሰን በክናየጘ አይርኒስ ኪርም ቅፋነል ጥዉጡዊል አሽ በክንቲስ ናጸ አቐዉ ጒደነዝ አኽቨነዉ ቸልሽጠ ማጥን ከቨዝመ ቲክንክነ ጻቨነዉዙ ሰቭድ አክንዉሻጙ ችጝሸኩ ይጘኩ
ዝቛለ ወረደ አርሽነይ ጽ/ጝንዙ አርሽነይ ጽ/ጝንዙ ቲክነተ ዲቈተ አት ጌትነት ከበደ ጝታ ጋቢዝ ወረደይል 2017/18 ጊቭርትዙ ዚምኒዝ ዲቈዉ አምረይስ ቺዝየዉ አቕንትዝ ጥወርድ አልት ወረደይዝጘን ኻሊሸዉዝ ቑጠ ኽወዝ ሺፍንሸነዉድ ጋልጽጝ እቀኽቭሪዙ ኹረዙ ወይትነይድ ደድሰናንስ ችጘቁ አርድ እጉርቲስ ጽይ ተረዉ ከቨከቭሽትንዝ ሰራሸነዉዙ ባኽልድ አሩሸነዉዝ ኮሪዝ አኽቨናንስ ሰራሽታጙ ችጝሸነዉድ ዊግትጝኩጙ።
ዉሸቭል ክንደጥዝመ እንቅ ተገተግሽትንድ አሩሸነዉዝ አኽቨናንስ ችጘቁ ኽወጥድ ኾይረዝ ፥ እንስሰንዝመ ጝኮርድ ኻይየዉ ስወይስ ጨቅሻየጘን ትኩርት ጻቭሽት ሰራሽታጙ አቓንድ አይነተዝም ጅውነይል ችጝሸቁ አቅምዝ ዝላቀቑ እቅድ ቀሰው ፃቨጥ ዉሸቭልድ አቭርዘነዉዝ አኽቨነዉዙ ቲግቭርድ አክንዉሸዉ አቐነዉድም ዲቈተድ ዋርዝጝኩጙ።
እገረ ጊቭርትዝ 30ላይስ ንየ ጊቭርት በክነኩ።እን አጉረዉ ምጽነ ጽየዉ ጊቭትዙ በክንትድ ጽይሸዉ አቐዉ ምጽነዝ ቃጽቭጠጘን ትኩርትዝ ሰራሸነዉ ጡዉሸኩ ይነ እጻ የጝ፡፡!
አመልማል ተድላ
ሚስኲሩም 15/2018