ዊግሽኒስ ጽፈሽል አሽ

አልምቱ ሲጘዝ እጅር ኹር ሚዝረ ላውጥውጥሸቁ እንዝጘም ጝ ኻሰቭድ ለምሰቁ ኽፅሙ ጒደንጢስ ላውድ ጋዜጠ የጝ።

ዚምነንዙ ፃጝትዝ እጅር ኹርዙ አዕምሮዝመ ኻስቨኻስቭንዙ ሊግዝትድ፣ ነን ችጘው ስልጣኒዙ ንየትነይድ ቲክን ጋዜጠ ዲቁ ተረቁ ጒደንጥድ አጝክርሰው የጝ።

አልምዝ ጋዜጠዙ ሲጘ አኰ አድለ ዚምኒዝ ንየ እጊስኲ።

እኔንት ሲሪየቊድም አውሮፓቊ አቕጘጘ ፅንኸን ሚሪየቁ አጘንድ ኪርመነ ጊዝዝ ጋዜጠ ፃፍሸውድ ናንዙ ፅፍሽዝ የጝ።

ጣይትንዙ ሚዝረይስ ኪርም፣ ኢኮኖሚዙ ኻለየን፣ ባኽሉ ቲግቭረን፣ ገረዱ ሚዝረንጢል አሽ ናንዝ ፃፍሽጝ ንየጥዝ ጅልውልዋጙ ቲኒታጙ ዊኑ።

14ትረ አድለ ዚምኒዝም ጋዜጠት ኪርመነ ጊዝዝ ማሽንዝ ኻትምረይ ኻግር ጀርመን ጚ። ቲክንም እንግሊዝ ጝርቕምቱ ቈንቈዝ ቅርፅዝመ ፃየድ ዚምንስራጙ፣ ፈራዘነው ቸልች።  1666 ዓ.ስ “London Gazette”ት ኻትመነውዝ ጝጉግድ ቃፅሉ።

ኢትዮጵየትልም ጋዜጠ ኪርመነ ጊዝዝ ሲሪሸውድ አጼ ምኒልክቱ ዚምኒዝ ብልቓጘ ቈንቈዝ ናንዝ ፃፍሽት ፈው “አእምሮ” ይሽተው ጋዜጠዝ  የጝ።

“አእምሮ” አፍሪከቱ ቈንቈዝ ኻትምሸው ኪርመነዙ ጋዜጠም የጝ።

ንቕፀቁ እምተንዝ እግርገም ኻትምሸነው ኪርመቁድ “አዲስ ዘመን” (1933) ጋዜጠስመ (1940) እንግሊዝኘዝ ኻትምሸነው ኪርመውድ “ኢትዮጵየ ሄራልድ (“Ethiopian Herald”) ጋዜጠንድ ጛይ።

አልምቱ ሊግዘቁ ኻግራን ጝተ ኽዝቭዙ ላውንትነይዝመ ሊግዝትዙ ምላሰንድ ኽትምትዙ ጋዜጠን ጛይ።

ጋዜጠዝ ኻግሩ ባኽልድ፣ ኢኮኖሚዙ ኻለየንድ፣ ገረዱዝመ ፓለቲኩ ኻለየንድ እንዝጘም እማንትነይድ ደድሽተቁ ሚዝረንጥድ እቀኽቭሪዝጎ ምርቅዘነውዝ እቀኽቭርድ ላውጠ ነው ቸልሽኲ።

እኒዙ ቓሊሰነም ቻይናቱ እፍርቲል ትኩርት ፃቨው ኪርመነ ጊዝዝ 1981 ዓ.ስ ሲሪሸው “ቻይና ዴይሊ” ጋዜጠ ላውድ የጝ። ነንቱ ሰቲዝ 1 ሚሊዮንስ ንየ ኽትምትዝመ 3 ሚሊዮንዝ ንየ ዲጂታልዙ አንቭቨጥ ፃይኩ።

15ትረ ላ አድለ ዚምኒስ ኪርም ብጭቕ እምተንዝ ኽትምትዙ ሚዲየን አይንተ ጂጘ፣ ትውፅውፅ (ዘናሸነ)ዝመ ክንድጝዙ ፍልፍለ አቕጝ ዊንጝኩⶔ።

አልም አቅቨ ተግዝ 20ትረ አድለ ዚምኒዝ ቴሌቪዥን ምልው የነውድ፤ 21ትረ አድለ ዚምኒዝ ቈሽ ዲጂታል ሚዲየዝመ ገረዱ ሚዲየንጥ ምልው የነውድ ቲክን ጋዜጠዝ ኽየው ፈተነ አቓጙ ተርኲ።

አቕሽም ዊርተ ፃየው ሚዝረዝመ አምንሸትነይ ፃየውድ ጋዜጠዙ ኽትምት አቓንስቅ ጋዜጠ ኽትምትዝመ ዲጂታል ቴክኖሎጂድ ቲክነነውዝ ጃፓንት ተከቁ ኻግረን ጋዜጠዙ ጝተ አንቭቨጥድ 7 ሚሊዮኒዝጎ ሊጊሰነው ቸልጝኩⶔ።

ኢትዮጵየት ፕሬስ ድርጅትድም ቓልናን እልቱ “አዲስ ዘመን”ስመ “ዘ-ኢትዮጵያ ሄራልድ”ት ቈሽ ላጥ ኻትምዘቁ ጋዜጠንድ ቅርፅዝመ ፃየዙ ልውጠ ፃቨነውዝ እጝቅ ኻግርሸንቱ ጅውንጢል ችጝሽተትነይድ ፈራዛጙ ችጝሸኩ።

ወይትጘድም “ላይ ጝርኘስ አረይ ኽምጠ ዊከ ጋዜጠ” ወይት ኽዝቪዙ ድመ አቕር 15 እምትድ እጊስርኩች።

ወይኽምረ ብሔረ እቅ ጭሰጭሰንል ኽምጣጘ ቈንቈድ 1988 ዓ.ስ ሰቭዝጎ ጥዋንስ ምኽር ጝንድ ፃድቅዘው አቓንድ “ኽምጠ ዊከ ጋዜጠ”ም  ጥቅምት 2003 ዓ.ስ ኽምጣጘዝ ፃፍሽር ኻትምሸነው ኪርምች።

ቈንቈዝም አቑ ጋዜጠዙ ኽትምትዝ ነንትል አሽ ወይቱ ባር አረይ ኽምጠ ዊከ ጋዜጠ ወይቱ ጅውነይዙ ፃጀድ፣ እፍርትዝመ ቀሰው ጭሰጭሰንዙ ችግሰንጥድ፣ ባኽልዝመ እሴተንድ ደመደምስራጙ ችጝሸች።

ንቕፀቁ ወይትጘም ክንደጢስ ኪርም ምሑረኒል(አርቐጢል) አሽ አጉረው ተምዝትዝ አንቭቭጛጙ ተርጝኩⶔ።

ኽምጠ ዊከቱ አንቭቨጥ ማኽሊስም አት ማረኝ ወ/ሰንበትስመ አት አብጨ በየነስ ኽምጠ ዊከ ኻትምሸነው ኪርምረት ኪርም አንቭቭጛጙ ተረቁ አቐነውድ ዊግትጝኩⶔ።

ኽምጠ ዊከ ጋዜጠ ወይቱ እኩስረው እኩሰድ ልብስጘንድም ወይትል ጋዜጠም አነ ላጥ አንቭቨነቁ ኽትምትዙ መፃፈን ዊኒጘው ኰሪዝ ጅውነይዙ፣ ክልሉዝመ ኻግሩ ሚዝረንጥድ ጝርጊስ ችጝጛጙ ተርጘጘድ ሚሪጝኩⶔ።

“ኽምጠ ዊከ ቀሰው ፃየንዝ አስልሽር ቈንቈድ ሊጊስረይ፣ ክንሰነውዝመ ዘናሰነውዝ ንቕፀቁ ሚዝረንጥድ አርቒስረይ ወይቱ ቃውሰተ ሚሪየ ጚ”ይጝኩⶔ።

ኽምጣጘ ቈንቈዝ ኻትምሽረይ ጋዜጠሸን እጝቅ ወይቱ ክንድጝ ጝንጥል፣ ሰራሸነ ጝንጢልመ ኒግርንዙ ችብረንጢ አሽ ችጘነውዝ ጅውነይዙ እቀኽቭሪዝመ ፅበው ኹርድ ጝ ሲጘድ አርቓንስ ክንስራጙ ተትረይ ጋዜጠ አረጘድ ጉይጝ ቈንቈዙ ሊግዝትዝም እኩስረው እኩሰድ አጉረው አቐጘድ ልብስጝኩⶔ።

ኽምጣጘ ቈንቈዝ ፃፈነውዝመ አንቭቨነው ቸልሸው አቐነውድ ኽምጠ ዊከ ሚሪየ ብዝረጘድ ዊግተቁድ ቈሽ አዲስ አበበ ኻትመይል ፅበቁ ወይቱ እኹርሸተ ኮማንደር ወንድሙ ገ/መስቀል ጛይ።

ኽምጠ ዊከ ጋዜጠ ኻትምሸነው ኪርምረት እጝጎ ንቕፀቁ ድዝጝ ዊነቁ ኽምጣጘዙ ቈንቁጥድ ዋጥርጝ ዊግሽጛጙ አቐነውድ አርቒስጝኩⶔ።

ኮማንደር ወንድሙ “ብልቓጘዝ ስጙርሽ ዊነው ኽፅሙ ኽምጣጘዙ ቈንቈድ ጉልምድ ፈነውዝ ወይቱ ባኽልድ፣ ሲጘዝመ እሴትድ ደመደምሰነውዝ ፅበው ኹሪዝ አርቕት ፋጥረነው ቸልድረይ ኽትምት ጚ”ይጝኩⶔ።

ኽምጠ ዊከ ጋዜጠ ተረዊዝ ወይቱ ሲጘዝመ ቈንቈዝ መፃፍ ፃፈቊዝ፣ አስጘ ችጘጢዝ( አስጘጢዝ)፣ ጅመጢዝመ ተረው ኹሪዝ ኽይረይ ሚዝረ (documment) አቕር ጎይረይ አረጘድ ልብስጝኩⶔ።

ኽምጠ ዊከ ጋዜጠ 13 እምተንዝ ቑጠ ኻትምሽር ኰሪዝ አንቭቨጥዝጎ ችጝራጙ ዊንድርሽም ሊጘ እምትዝ እጝጎ ፅበው ክልሊዙ ፃውተዙ ችግሰይዝ ምላሰን አንቭቨጥዙ ናኒል ኽትምትዝ ችጘነው ቸሊረይም።

እንዝም ጝር አንቭቨጥድ ብራጙ የጝ የነው ቸልሸኲ።

አት ማረኝስመ አት አብጨቱ ኻሰቭድም አንቭቨጥ ፅቃች ጨቨቅ በንትዝ ኻይጘይ ኽምጠ ዊከ ጋዜጠት ኽትምትዝ በነው ተረው ኹሪዝ ሚዝረ ድሰነዊዝጘድ እጊተው አቐነውድ የጝ ሚሪጘውድ።

እንዝጘም ቈሽ አንቭቨጥዝ ሲለሳው አቕንትዝ እጅጝዝመ ካኽተዝ ፃፈነው፣ ድቃል ሆህየንድ ጥውጘው ስፍረድ ቺዘነውዝ ተረው ኹሪዝ ጭቅቱ ቈንቈዝመ ሲጘ ከሰነው ጥውሸው አቐነውድም ኻስቭዝጝኩⶔ።

ኮማንደር ወንድሙም አቕሽ ተረዊዝ ብላ ሚዲየ ኮርፖሬሽንድ እቀኽቭሪዝመ ሚሪሸቁ አካለንጅቅ አቨርድ ወይትል ችጝሽትየቁ ጅውንጢል እቀ ኽቭሪዙ ፃጀድ፣ ባኽልዝመ ቀሰው እሴትድ ኽትምትዝ ፊሰነው ጥውሸው አቐነውድ ኻስቭዝጝኩⶔ።

ጋዜጠ አንቭቨጥ ጋብዝ እማንትነይድ ደድሽተው አቕሽም ቺተዝ ቈሽ ገረዱ ሚዲየ( ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ኢንስታግራም፣ ዩቱብ) ተከቁ ዲጅታል ሚዲየንድ ፃየዝመ ቅልጥፈዝ ፊትንሻጙ ችጝሸኩ።

ብላ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ኽቭር ኽምጣጘ ዳይሬክቶሬትዙ ዳይሬክተር (አስለተ) ጋዜጠኘ ወንድሙ ቸኮለ ጝተ ጋብዝ ኽምጠ ዊከ ጋዜጠ ጝር ዊርተዝመ ችጝሽተትነይድ ሊጊሰናንስ ሰራሽታጙ አቐነውድ ሚሪጝኩⶔ።

“ኽምጠ ዊከ ጋዜጠት አፅቨነው ቸልሻውም፣ ላጥ ሚዲየንጥዙ ዲዝጝትድ ፊስን ጝርቕምቱ ትንዝንዙ ሙየ ጉሪየ ችበችብሰነውዝ እጝቅ ጅውንጢል ኽትምትዝ ችጝር አንቭቭሽተጘድ አሚኮ ሰራሻጙ የጝ” ይጝኩⶔ።

ጋዜጠ እቀኽቭሪዙ ሲጘድ፣ ባኽልዝመ እሴትድ ተረው ኹሪዝ ከሰናንስ አጉረው መሰሪ አቐነውድ ዊግተቁድ ጋዜጠኘ ወንድሙ እጅጝ፣ ዊርተዝመ ካኽተ ፃይረይ ፃቭን ፊሰነውዝ አንቭቨጢዝጎ ችጝዘናንስ ኻሊጝ ሰራሽጛጙ አቐነውድም አርቒስጝኩⶔ።

ጝር ችጝሽተትነይድ ፈራዘናንስም አቭርደቁ አካለንዝመ ብሔረእቅ ጭሰጭሰኒዙ ምኽር ጝንጅቅ አቭርድጝ ሰራሸቁ አቐነውድ አርቒስጝኩⶔ።

ጋዜጠ አንቭቨቁ ክንደጥ አትረው ቃለንድ ጉልምዝጘኩ፣ ዊገ ፈውሰነዙ ፅረፅርሽንዝም ቺዝየው አርቕት ፃይጘኲ።

ጋዜጠ አንቭቨነውዝ ቺዝየው ኻስቨኻስቭንዝመ ቈንቈዙ ቸልትድ ሊጊሰነው ጥውሸኲ።

አስትውልንዙ ቸልትድ ሊጊሰነውዝ ችግሰንጥ እክሰነውዙ ዲዝጝትድ ተረውድም ኽትምትዙ ሚዲየ አንቭቨናንድ የጝ።

ሳምራዊት ግርማይ

ኽደር  15/03/18

- Advertisement -spot_img
- Advertisement -spot_img

Latest article

AMECO Himitgna