ፍጥርት ቃጽልጠጘ…

ዓልምትል እትላጙ ፅበው አየርዙ ልውጠድ እሩዘነው ጋብዝ ዘፈን ፃይጘው ችጘርድ አጉረው የጝ ። ደን ሚንምንሸነዊዝ ምላስንዝም አልምቱ አየር ንቭርትድ ላውጥውጥሻጙ ፤ ኽረዝመ አጉረው ብርትዝ ዓልምት ፊትናጙ  ችጝሸኩ ። ቺተዝም አውጭለ (አውሎ ነፋስ) ፣ አቝዙ ኰስየ ፣ ሊየዙ ቃጥልን ፣ አጉረው ኩረዝመ ዝቨዙ ኒንቅሽን ተከተከቊ ኻደግጥድ ዓልም ፍራትዝ አቭኑዝራጙ ችጝሸች ።

እንም አቐነዊዝ እጅር ኹርድ ቈሽ ንቕፀቊ እሩሄ ፃየቊ ፍጥረታን ጝታሩሄድ ኻደገል ሊቫንድ ቓልሽተኩ ። እኔን ችግሰድ እዳዘናንስ እድወ ኻግራን ጝታይታ ሚልክ ዝቨይዝመ አየር ንቭርቲዝጘድቅ ቲስመመቊ አፅዋተንድ ቲክለነውዝ አየር ንቭርትዙ ሉጠድ እሩዘናንስ ሠራሽጛጙ ችጝሽጘኩ ።

ይና ኻግር ኢትዮጵየም 2011 ዓ.ስ ኪርምር “አልቛዘዙ ደፈዝ” አጉረው ጊንዝቭ ፊስር ፣ ንቕፀቍ ፍለንድ ፍልዝረጙ  ጫረ ጨቨቅ ቲክልሽጥጘጘ ፃቭራትቅ ችጝሸች  ።

2011 ዓ.ስ ፍለን ቲክለነውዙ ሰቭድ ዝምረዝ ሠራሽተነው ኪርምሸው ኮሩዝ ላው ግሬዝ 3 ላዝ 50 ሚሊዮን ፍለኒስ ንየ ቲክለነውዝ ህንድስ ፃይሽ ዊነው ንየትነይድ ፊሰነው ቸልሽኩ፡፡

2016 ዓ.ስ አልቛዘ ደፈዙ እፍርት  ቃወ ግቭሪዝም ኢትዮጵየ በንዘው ቃውሰ አስለንድ አስራጙ ችጝሸች ። እኔንትም ቲክን 2016 ዓ .ስቑርትዝ 6 ነቁጠ 5 ቢሊየን ፍለን ቲክለናንስ አስልሽን ፃቭሽተነውድ የጝ ኢትዮጵየቱ ጂጘ አግልግለድ ዚግቨውድ ።

እን አምረይዝ ቲክልሸቍ ፍለኒስም ጥቅለተ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ይውጘው ሚርየድ ሲርየ ፃቨነውዝ 60 ላይስ ፃምርሸው(ጥምር) አርሽነይዝመ ፍረምረንዝ ፤ 35 ላይስ አቐውድ ቈሽ ደንዙ እፍርትዝ እንዝጘም 5 ላይስ አቐቊድ ቈሽ ገይፅዝ አቐቊ ፍለን ቲክልሸቍ አቐነውድም አርቕሽትኩ ። እን ኻለይድ እሩዘናንስ እድወ ኻግርዝጘ 70 ሽኽዝ ንየ ፍለንዝቊ ጣቭይጥል ሰቭድ ሰራሽተጙ ችጝሸኵ።

አልቛዘ ደፈ እፍርትዙ ሰቭድ ወይ ኽምረ ብሔረ እቅ ጭሰጭሰኒዝጘድ ማጥማጥደቍዝመ ደግምግመዝ ኽረድ ጣዘቊ  ጁንጢል ቈሽ እውግረው ትኩርት ይውሽት ሠራሽትጠ የጝ ጡሸውድ።  እኔንት ቲክንም ብሔ ‘ቅ ጭሰጭሰኒል አምረ ጨቨቅ ንቕፀቍ ችግኛን ቲክልሸጘኩ ። ውርም እንኳ ችግኝዙ አርወድ ላው ግሬዝ ቓልሽተው አየው አቕሽም ቲክልሸቍ ችግኛኒዙ ፃድቀነውዙ (ፃየነውዙ ) ምፅነድ ግነ አምረይስ አምረ ቲስፈ ይወው አቕንዝ ቓልሽታጙ ፤ እቀ ኽቭርድም ቲግቭርድ አርወው አቐነውድ ልብት ላብጠትቍ ቅብረጢል (ድርዝ ይሽትጝ ኪልክልሸቍል ) ፤ መንግስትቊም አጝነ እምንትዝቍ ችብረጢል የውም ጝታይታለቱ ጝን ግረይል ወይም ቺዝጝ ደዪይል ሙየ ጒጥዙ ምኽር ኻሰቭድ ለምርን ቲግቭረነውዙ ሰቭድ ግነ አምረይስ አምረ አትራጙ ተርኩ ።

ቺተዝመ ዲቀ ወረጢል የነትም አምደ ወርቅ ኻትመ ጭሰጭሰን ፣ ድሃነ ወረደ ፣ ጋዝጊቭለ ወረደ ፣ ሰቊጠ ኻትመ ጭሰጭሰንዝመ ሰቊጠ ወረደ አንፃሩ አቐው አቕንትዝ ቺዘው ችግኝዙ ፃድቀነውዙ ( ፃየነውዙ) ምፅነ ፅበነውድ ብሔረ እቅ ጭሰጭን ደንዙ ቃወነድ ነየው ሚዝረይዝ ልብተነው ቸልሽኩ ። ቺተዝም 2015 ዓ.ስ ቲክልሸቊ ችግኛንድ ፃድቅዘነውዝ ጋብዝ ቀሰው ዲዝጘ ፃየው የጝ ይሸተው ወረደድ ድሃነ ወረደድ አቐነውድ ብሔረ እቅ ጭሰጭሰን ደንዙ ቃወነይስ ሚዝረድ ጕይን ጝታ ዲዝጘድ ውር ተከጘዝመ ተረቲዝስ ሰራሽጘው ሰቪስ ቺዘው ዲዝጘ ፊሰነውዝ 2016 ዓ.ስ ሰቭድ አትርዘናንስ ፃይጘው ኻለይድ ውር ተከጘድ ችግኛኒዝ ወነዝመ ታኽንኽነተ አቐቊ እቀ ኽቭርዝ ክፍላኒዝጅቅ ስልክዝ ዊንተ ፃቭን ቲክነው ክንሰተ አቐው ጝታ ኻሰቭድ ነይጝኩጙ ።

አት ገበየሁ ነጋሽ ድሃነ ወረደ 03 ቀቨሌ ፅበተ ጛይ ። ችግኝ ቲክለነውዙ ሰቭድ ቃውስ የቊ እምታኒዝቅ ቲክልጛጙ ተርጘጘድ የጝ ጋልፅጘው ። አቕም ግነ ዲቈቍ ሊጘ ሻቘ እምተኒዝ ፋጥርሽ ዊነው ጣይተኒዝ ቅብረጥድ ሸርሽጝ ንቕፀው ቃነማነ ድዘነውድ የጝ ጋልፅጘውድ ። ድዘው ፍጥሩ ፃጀድ ዊነዊዝጎ ዊሰናስ ዊሰናንስ ሰራሽተቍ ሰባኒስ ላውድ አምረ ጨቨቅ ጫረ ጥወነይዝ ኝግኝ ቲክለነው ሰቨድ ላውድ የጝ የቍድ አት ገበየሁ ” ዲቍስነው አምረይዝ ቲክልነቍ ፍላንድ ፃድቅጛንስ ሚስክርምስ ኪርም ለካቲት አጢስ አድልድልሽን አቘ ዚስናጙ እንቅ ቲክልሸቈ ችግኛንድቅ ፃድቅጥጘ ፃቨነው ቸልንኩኑን ” ይጘኩ ።

ላውላው ጛሉ አርወድ ቃውሰቍ ጛልቍ እቅ ኪልክልሸው ደንዙ ዝቨድ ሸራይጘጘድ ዘቨኝጥ ቃፅርሽጝ ፤ ቺዝጠ የውም አነ ቀር እንሰስ ድወው ፅብሽ እቀ ኽቭርድ እቑረው ቕፃር ፅባንስቅ ጝዝ ልክ የጝ ቐፃሸጘውድ ። “ችግኝ ቲክልሽ ጁነድ ድርዝ ሺፍንሻንድ አርውድ ይናው የጝ ” የቍድ አት ገቨየሁ ነንም ተረው ጫረይዝ ቲክልሸቍ ችግኛኒዝ አቐው ቢጙ ፃረነው ሰቭድ ሰራሽጛጙ ላብጠቱድም አነ ጛሉ ችግኝ ቲክለ ሰቭድ አክኑጛጙ አቐነውድ የጝ ጋለፅጘውድ ። ላየ ቓለ ነየቍድ ዊዝር ብርቱካን ወዳጅ ይሽተቍ 03 ቀቨሌ ፅበተ ጛይ ።

እጅር ኹር ጝኹርስ ቃፅልዝ ታኽንኽንጠ ጡሸውድ ዘፈንድ አጠ ጡሸኩ ። ምላሰንድም እጅር ኹር ጭቅተዝም አነ ጅሉሉዘዝ ጝፅብንድ ሲሪሸውድ እንዘፈኒዝጅቅ የጝ ይጘኩ ። ዲቊስነቍ እምታኒዝ ቲክልነቊ ፈላንድ ነን ፃመ ማለው ዝፍዝጎ አልትጝ ቓልጛንድ ጝታ ሚንፍስድ እምጥጘዝ እቻቓጙ አቐነውድ ዊግተቍድ ዊዝር ብርቱካን፤ ” እኔን ቺትየው ገቨድ ቓልነ ቸልነውድ ፍልድ ቲክልጥን የጘው ኮሪዝ ቲክልን፣ ኢዛይጘጘድ አቘ ዚስናጙ ጡሸውዝ ታኽንኽናንስቅ የጝ’ የቊ አጛንድ ፥ ዲቀድ ቆለይዝጘ ሸልቅዘውድ ቅነማነድ ድዘነዊዙ ላው ቓሊሰነ አቐነውድ ልብተነው ጡሸኩ ይጘኩ ።

ተረው ጫረድ ጡነዊዝበውግ ፍላን ቲክለናንስ ማርሽተቍ ቅብረጢል ቢጙጣን አስለነውዙ ሰቭድ ቀሰው አቕንትዝ ኪርምሸጘድ ጋልፀቍድ ዊዝር ብርቱካን “ሰራሽነው ሰቭድ ቓዘውድም ቖይዘውድም ይናት አቓንስቅ ፤ ጁነድ ማጥማጥደነዊስ ቓዝናንድ ነየው አርወድ ኻስቭናጙ ሰራነ ጠሸኩ ” የነውዝ ማኽርጝ ፤ ጉልወድ ቺዝጚል ውላቓንድ እውነሸን ፤ እውነሸንስ ጝንዙ ሰቭድ ንቕፃንድ ጉልውድ ታኽንኽነ ይውሽተቍ ችግኛንድ ጡሸውዝ ታኽንኽንን ሊጊሰነውዙ ዲዝጘድ ዘስክርሽጠ ጡሻውም ። እንሰስም አጝነ ላጥ ቅብረጢል ጡዋይጘጘዝመ ዘፈንድ ቀቭሽታይጘጘድ ኻየነውዝ ጋብዝም ቃፅርሸቍ ዘቨኝጢዝ በረነው አቒጝቀት አውማው እጅርድቅ ጝሉ ቺዝጚዝጘድ ፃቭ ቓለጠ ጡሸኩም ይጘኩ ። ዊዝር ትዕግስት መንግስቴ ድሃነ ወረደ ጁነ ሊሚስን ፅፈሽ ጝን ዲቈተ ጝታ ጋቢዝ ድሃና ወረደድ ችግኝ ቲክልዝን ፃድቅዘነውዝ ጋብዝ አምረይስ አምረ ቀሰው ዲዝጘ ቓልሽታጙ ተረነውድ ጋልፅጘኩ ።

ጝታ ችብረድ አርሽነይ ፅፈሽ ጝን፤ ሚንወዝመ ቈልቍ ጁንጥ ፅፈሽ ጝን ፤ አመልድ ኢትዮጵየ ላውንዝ አቕን ሰራሸነውዝ ችግኝ ቲክለነው ጭቝ አቒንቀት ቲክልሸቍ ችግኛንድ ሊጊሰናንስ ሰራሽተው ሰቭድ ቀሰው ሉጠ ቓሊሳጙ አቐነውድ ጋልፀቊ ዲቈተሸን “2016/17 ዝ 3 ሚሊዮን ችግኝ 8 ላዝ 45 ሄክታር ዝቨል ቲክለናንስ ኻለይ እቑርን ነንአጢስ 2 ሚሊዮን አጥጘ ፍለን ፍልዝንኩኑን” ይጘኩ ። እንዳይ ፍልደቍ ፍላንድ አወየን ፍልድ አውል ቲክልሽጠ ጡሸጘዝመ ፍላንድ ቲክለናንስ ቸልሰቍ ጉድጓደን ፃረነውዙ ሰቭድ ግንቭት አሰነይስ ኪርም ነን አጢስ ሰራሽናጙ ቃውሰ አስልሽንዙ ሰቭድ አሰነውል ችጝሽነኩንም ይጘኩ ።

ዲቈው አምረይዝ ቲክለሸቈ ፍላኒዙ ፃድቅንዙ ምፅነድ ቓልሽታንደ 78 ለይስ አቐነውድ ጋልፀቍድ ዊዝር ትዕግስት እኔን ፈንድ ሚዝግቭዘናንስ ቸልሰውድ ወረደይዙ እቀ ኽቭርድ ቲክለነዊስ ኪርም ችግኛንድ ጝታውር ቸልጝ ኮረድ ማኽተነው ቸልጥጙ ደረጀይል አሽ “አቘ ዚሰነውዝ ፤ ኲትኩተነውዝመ አርመይስ ናፀ ፃቨነውዙ ሰቭድ እን አምረይዝም አትርዝን ቃፅልዘነውዝ ቲክልነቍ ፍላንድ እንቅ ፃድቅጥጘ ፃቨነውዙ ሰቭ ሰራሽነቅ አነኩን ” እኔንት ፃቨናንስ አውማው እቀ ኽቭርድቅ ሙየ ጉርየ ይወው ምኽር ኻለይድ ለምርን ቲግቭርል ግሪሰነውዝ ጝታወረደድ አልቛዘ ሲናንስ ሰራሽጠ ጡሸጘድም ኻስቭዝጝኩጙ ። ጛልቍም አጝነ መንግስትቍ ችብረጥ የውም ፣ እምንትዝቍ ስፍልዝመ ክንድጝ ጝንጥ ጝታይታ ኻፅር አቒል ችግኝ ቲክለነውዝ ኻግሩ እፃድ እሩዘነውዝ ጋብዝ ጝታይታ ችጘርድ ፍነው ጡሸኩም ይሽትኩ ።

ወይ ኽምረ ብሔረ እቅ ጭሰጭሰን ጁነዝመ ደን ኻይሰነ ቃወነይዙ ደርግቭሸተ ዲቈተድ አት ዓለሙ ተዘራ ነይጘው ጋልፀነይዝ ብሔረ እቅ ጭሰጭሰንድ 2015/16ይዝ 3 ነቁጠ 1ሚሊዮን ችግኝ ቲክለነውዝ 2 ነቁጠ 25 ሚሊዮን (68•6%) አጥጘ ችግኛንድ ፃድቀነው ወይም ፃየነው ቸልጘጘድ ጋልፅጝ ፍላንድ ፃድቅጛንስ ቸልሰው ቲግቭርድ ቈሽ “ይና ችብረድ አርሽነይ ቃወነይዝጅቅ ፣ ሬድ ፕላስ የሽተው ቀሰው ፃቨተ ድርጅትዝመ አመልድ ኢትዮጵየጅቅ አቭርደነውዝ ሴፍትኔት አሩሸጥ ችግኛንድ አቘ ዚስጛጙ ታኽንኽንጥጘ ፃቨነውዝመ ላየ እቀ ኽቭርድ ቈሽ ጡሸውዝ ኻይጠ ፃቨነውድ የጝ ” የነውዝ ዊነው ዲዝጘድ ጋልፅጘኩ ።

አት ዓለሙ ፃየፃይሰነውዝም ወይታት ተከቁ ማጥማጥደቍ ጁንጢዝ ችግኝ ቲክለነው ማርፀ እጀው ቲግቭር የጝ የቍ አጛንድ 2016/17 ዓ.ስ 5 ነቁጠ 8 ሚሊዮን ችግኝ ቲክለናንስ ኻለይ ፃይሸጘዝመ ነን አጢስም 1 ሽኽዝ 8 ላዝ 71 ሄክታር ዝቨል ቲክለናንስ 4 ነቁጠ 5 (78•5 %) ፍላን ፤ አስልሸቍ አጛንድ፤ ነን አጢስም 2 ሚሊዮን 1 ላዝ 86 ሽኽዝ 9 ላዝ 87 ቢⶓን

አስልሸቍ አቐነውድ ጋልፅጝ “እቀ ኽቭርድ እዳቐቍ ጉድጓደንድ ፃረነውዝ እስወ ሊቨነው ኪርመው ኮሪዝም ችግኝ ቲክለነውዙ ሰቭድ አትርዝ ቃፅልዝጠጘድ ኻስቭዘኩን” ይጝኩጙ ። ችግኝ ቲከለነውዝ ፍጥሩ ፃጀድ ታኽንኽነነው የነት ሩሄ ቃፅልጠ ፃቨነት የነት የጝ ። አቓንስቅም ወይት ትርጥድ አልቛዘዝ ሺፍነነውዝ ዚሩ ሚክርሸተ አቒጝቀት ዚሩ ሚክረተ እቀ ህቭር ፋጥርሻንስ ሰራሽትነ ይና አስለ ክፍሊዙ እፃ የጝ ።

ዚግቨተ ንጉሱ ማሩ

- Advertisement -spot_img
- Advertisement -spot_img

Latest article

AMECO Himitgna