አ.እ 2017 ዓ/ስዝ አልምቱ ትኽነ ድርጅት (World Health Organization)ድ ፃቨው ፅንኸ ቓሊሳንትጘድ 2 ሚሊዮንዝ 95 ሽኽ አቐቊ እቁን ጊዙርንዝመ እኹርንዝ ኰሪዝ ጝታ ሩሔድ ዲቊኩ።
እንዛግስም 94 ላይስ አቐቁድ ሊግዝጛጙ ፅበቁ ኻግረኒል አቐነውድ ዳጝጊፅሰኲ። እን አቕንቲዝሰሃራት ሳ ፅበቁ አፍሪካት ኻግራኒዝ ጭቑ 1 ላዝ 96 ሽኽ ኵየንጣንዙ ክርጘ ሚዝግቭሽኩ። ይና ኻግር ኢትዮጵየም 14 ሽኽ ኵየንጣንዙ ክርጘ ሚዝግቭስርኩች።
ኢትዮጵየትል ኵየንጣንዙ ክርጘይጅቅ ፃየፃይሽት ፅንኸ ፃቭሽትኩ። አምረይዝ ክረቁ ኵየንጣን 50 ላይስ አቐቊድ ብር ቅብረነውጅቅ ፃየፃይሸው አቐጘ ጋልፅሽትኩ።
ኢትዮጵየ ዲቈቁ 15 እምታኒዝ ጝነቁዙ ምፅነ አገልግለ አሩሸቁ ኵየንጣንዙ ምፅነ 27%፣ቃውሰ እኹርንዙ ቲክንክነ ፣56% እንዝጘም ትኽነዙ ችብረል እኹረነውዙ አግልግለ ችጘቁድ 22% ንየስ ሸነው ቸልሸጘ ሚዝረን ቓሊስጘኩ።
1990 – 2015ዓ/ስ አሽ ኵየንጣንዙ ክርጘ ልውጠ ቓሊስሽም፤እፍሰው ግነ አየውም። ፈንድ ኢትዮጵየቱ እፍርትዙ ፈንጥ (Millennium Development Goals) ኻሊሽተዊዝ ሳ ሚዝግቭሸነውድም ተረቲስ ስራሽትጠ ጡሸው አቐጘ ቓሊሰነ የጝ።
ወይ ኽምረ ብሔረ እቅ ጭሰጭሰን ቈሽ ገቭድቅ ወረጘኲ፡፡ ንጭቱ ይና ገረዱ ዲቭየይዝ እደስየ ኲየንጣን ክርጘድ ቃፅቨናንስ ጊዝውርቲስ ኪርም እኹርጢስ ፃቭሽተው ቱክንክነዝመ ከቨድ አምድወርቅ ኻትመ ጭሰጭሰንዝመ ድሃነ ወረደይዝጐ ጭቅ ይን ችጝነው ሚዝረድ ደምደምስነ ቀንኑን፡፡
አምደወርቅ ትኽነ ጣቭየ 1990 ዓ/ስ የጝ ሲሪሸውድ። ጝ ስሪል 35 ሽኽዝ 5 ላዝ 34 እቀ ኽቭር አድላኒዝ አግልግለ ይወኩ።
ፃይሸው አምረይዝ ነንትል አሽ ጥቅለ ትኽነ ጣቭየይል ቲክንክነ ፃቨቁ ኵየንጣን 9 ላዝ 85 ጛይ። 2 ላዝ 50 ኵየንጣን ትኽነ ጣቭየየይል እኹርጝኩጙ። ሆስፒታል ፊርጝ እኹረቁ ቈሽ 3 ላዝ 85 ጛይ። ሚዝግቭሸው ክርጘድም ላው ድድመ የጝ።
ዊዝር አታላ ጌትነት 031 ቀቨሌ ፅበተ ኵየን ጚ። ቃውሰ ጊዙርንዙ ቲክንክነ ፃቭራጙ ዊንድርኩች።አሰነይዝ ግነ ዊትርቅትጘድ ደድስተ ጝር ልኩዝ ፊረነውዙ ግርቭ ችጚረይም።
አምደወርቅ ትኽነ ጣቭየ እኹረናንስ ቃነ ቃሪዘዝም መውርሽር ፊትርኩች፤ አነጚ ጊዙትረውድ አቅቭን እምቘናንስም አነ ሲግሰይል ጅሉዝን በወናንስ ታድልሺረይም።
“ያን አጋሊዝጘ ቅዳን ሲቭንትጊርቀቱ 10:00 ሰቲዝ ቅምት ፃይጩን። ሳልጥም አምቡላንስ ለምራንስ ስልኪ ጣዙን፤ አነጚ ዊሰ ችጚቀርም” ይርኩች።
ቅዳን ሲንውትስ ኪርምር ሲኑ አሽ ቅምትል ሳብጥርኩች። አሰነይዝ ዝላራንድ ግነ ቃነ ቃሪዘዝ መውርጝ ትኽነ ጣቭየይል ችጝዘነውድ ሲጘ ጉርየየን ዋርዘች።
“ያን ነን ነቃቓንድ ፃይጨ እርፍ ግርቅ እግዘው ይኹርት ብኩን።እቀጘም ኻዝንኩን፤ኰሪዝ ትኽነዙ ችብረይል ተጣን ያንም ፅዊጢጝቀት ይኹርትም ትኽነዝ ችጝጨ ዊኑን” የነውዝ ዊዝር አታላ ጋልፀች።
“አምቡላንስ ትኽነ ጣቭየይል ጐይጠጘ ፃቭሽታቅ የውድ ዲግዙ ችግሰይዝ የጝ። ፍለውልወን ኵየንጣንድ ነሰናንስም አነ መኪንጥድ ኻሊሸው አለመይል ግርያየጘድ ችግስኩ” የቁድ አምደወርቅ ትኽነ ጣቭየ ደርግቭሸተ ዲቈተ አቐቊ አት አወቀ ምስጋናው ጛይ።
ወረደይል ላው ቃውሰው ሆስፒታል ፣ዋልጠ ትኽነ ጣቭየንዝመ 31 ትኽነ ኬለን ችጝሽጘኩ። 147 ሽኽዝ 144 እቀ ኽቭር አድለዝ አግልግለ ይወቁ አጘጘም ጋልፅሽተኩ።
አት ሞገስ አራጌ ድሃነ ወረደ ትኽነ ፅፈሽ ጝን ኵየንጣንዝመ ውሸብል ስነ-እኹርን ኦፊሰር ጛይ። ወረደይዝጘ አግልግለ ይወቁ አምቡላንሰንድ ሻቘ አቕጛንድ ፃውተይዙ ችግሰዝ ምላሰን ጛይም አውልም ፊርጝ አግልግለ ይዋቁም። ኰሩ ግደጅ ይውሽትጝ ፊረቁድም ዋጥርየቁ አቐነውድ ጡሸው አግልግለ ይዋይጘጘ ፃብሽተነውድ ዊግትጘኲ፡፡
“መኪንጥድ ኻሊሽተው ዓለመይልም ግርያየጘ ኰሩ ፃውተይዙ ችግሰድ ፊትናጙ የጝ። ቀቨሊ ጨቨቅ ፊርን ኵየንት ነሰናንስ ሚኩርሻውም። እንዝም ሲሪየ ዋልጠ ኵየንጣንዝመ 18 ድድም እፈር ክርጘ ሚዝግቭሽኩ” ይጛንድ ሙየ ጉርየድ ዊግትጘኩ።
ፃይጨትረ አርፈ ኪርመቁ ኵየንጣን እንቅ አምቡላንስ ኻይጝቀ ቃውስጝ ትኽነ ችብረንጢል ችጝጥጘ ማጥን ክንድጝ ይውሽተው አቐጘ ጋልፀቊ ዲቈተድ፤ ተፈራ ሀይሉ ጥቅለ ሆስፒታል ሪፈር በርሰናንስም ችግሽትጛጙ አቐጘም ዊግትጘኲ፡፡ ምላሰንድም ጊርቀ አቕየውዜ ኩኑቱ 12:00 ሰቲዝ ኪርም ግረቨዝ 12:00 ሰቲል አሽ ኰሩ ቕየድ ፍልውልወ ጊግቨው አቐነውድ ጉይሸኩ።
“ድሃና ወረደዝጘ ኰሩ ፃውተይዙ ችግሰይዝ ምላሰን ጊዙረቁድ ቺዘነው፤ሻቘ ሰቭል ፅበቁ መኪንጥ ፃለት ቃጥለነውድዝ አምቡላንስዙ አግልግለ ይወነው ቸልሰው አቕንት እጀው አቐጘ ጉየቊድ ቈሽ ወይ ኽምረ ብሔረ እቅ ጭሰጭሰን ትኽነ ቃወነ ዲቈተ አት አሰፋ ነጋሽ ጛይ።
ብሔረ እቅ ጭሰጭሰኒዝጘ ፃይነው ፃይጨ እርፊዝ 21 ኵየንጣን 73 ድድም ክርጘዝ ሚዝግቭሸነውድ ውንሰቊ አት አሰፋ ነጋሽ።
ክርጘይዙ ምላሰንድም ትኽነዙ ችጝቱነይ ጣቀቲል አገልግለ እጀው አቐነው፤ቃውሰው ሽልዙ ቲክንክነ ፃቨቅ የነው፤ኾነኾንዙ ስረት፤ሙየይዝ ጊውርሸው ስፔሻሊስትዙ እጅጝት ፅበነውድ ችግሰድ ቓቪታየጘ ፃቨቊ ቓመጥ አቕጘጘ ዊግትጘኲ፡፡
“ኽረ፣ ጣይትን፣ ሽወ፣ ፊንቅልሸተ ቈሸቈሽትጝ በንነውድ ቚጠ ተግረነው ቸሊነቅም”የቁድ አት አሰፋ ኵየንጣንዙ ትኽነጅቅ ፃየፃይሸውዝ ምጝግስትቚ አየቁ ድርጅተን (Non Governmental Organization) ዝ 80 ላይስ ምጝግስትዝ ቈሽ 20 ላይስ በጀትዝ ከቭሽተው አቐጘ ጋልፅጝኲጙ።
ኲየንጣንዙ ክርጘ ቲክንዘቚ ሻቘ ስኻርድንዝቚ ሞዴለን (The Three Delays Model) ይሽተነውዝ አርቕሽተቁድ:- ኽክምነዙ አግልግለድ ችጘናንስ ውሳኒድ ስኻርዘነው፤ ኽክምነይዙ ችብረይል ችጘናንስ ስኻርደነው፤ እንዝጘም ኽክምነ ችብረይል ችጝጘት ጡሸው ኽክምነዙ አግልግለ ችጛይነው የቊድ አቐጘጘ ልብተነውዝ።
ምጝግስት አየት ከቨጥ ድርጅተን እንዝጘም ሚሪሸቁ ምጝግስትዝቚ አካለን ችግሰድ ቓቭዘናንስ ትኩርት ይውጝ ሰቭትጝነ። ጋዜጠሸንቱ እፃ የጝ። ዲግ አጥን!
ዚግቨተ ፡- ኪሮስ ወልደ ተንሳይ
ሲን 30/2016 ዓ.ስ