ባሕር ዳር: መጋቢት 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ላስታ እና ቡግና በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ጎልተው ከሚታወቁ አካባቢያዊ ስሞች ተጠቃሽ ናቸው።
በወረዳዎች በተለያዩ ሥርወ መንግሥታት ዘመን የተሠሩ በርካታ መካነ ቅርሶች እንደሚገኙ የአማራ ክልል ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ መረጃ ያሳያል።
ከላሊበላ ከተማ በቅርብ ርቀት ከሚገኙት እነዚህ በርካታ የመስህብ ቦታዎች መካከል ለዛሬው ነአኩቶ ለአብን ገዳም እንቃኛለን።
የነአኩቶ ለአብ የዋሻ ውስጥ ገዳም በላስታ ወረዳ ከላሊበላ ከተማ ደቡብ ምሥራቅ ሰባት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
ገዳሙ ተፈጥሯዊ በኾነ ዋሻ ውስጥ የሚገኝ ነው። መግቢያው በጥርብ ድንጋይ የታነጸ እና ወደ በሩ ለመድረስ የሚረዳ የድንጋይ ደረጃ አለው።
በገዳሙ የሚገኙ የተለያዩ መጠን ያላቸው የተፈጥሮ የድንጋይ ገበታዎች ከቤተ መቅደሱ ጣራ በሚንጠባጠብ ፀበል ዘወትር የሞሉ ናቸው።
በእቃ ቤቱ ውስጥ ደግሞ የተለያዩ ነገሥታት ስጦታ እና የክብር እቃዎች፣ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት፣ “ስማ ጎንደር” በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ትልቅ ከበሮ እና ሌሎች ቅርሶችም ይገኛሉ፡፡
በገዳሙ ውስጥ በዘመኑ የተሠሩ የጨርቅ እና የገበታ ላይ ስዕሎችም ይገኛሉ።
ሥዕሎቹ የድንግል ማርያምን ምስል እና የክርስቶስን ስቅለት የሚያሳዩ፣ የቅዱስ ነአኩቶ ለአብን ንግሥና ገድል የሚዘከሩ ኾነው በወፍራም የውኃ ቀለም የተሳሉ ሥራዎች ናቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!