👉ከደሴ ከተማ በስተደቡብ በ5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከጀሜ ኮረብታ ባሻገር፤ በጦሳ ተራራ ሰንሰለት ጥግ፤ ከወረብቾ ተራራ ስር ትገኛለች፡፡
👉በተፈጥሮ ልምላሜዋ፤ በረግረጋማ ሜዳማ መሬቷ፤ ከዓመት ዓመት በሚፈሰው የገራዶ ወንዝ እና የቢለን ምንጭ ውኃ፤ በአበቃቀሉ ልዩ በኾነው የጥንቅሽ አገዳ እና በለጋ ቅቤ ምርቷ እንዲሁም በለምለም ቄጤማዋ ትታወቃለች።
ምንጭ:- የአማራ ክልል ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ