የመስሕብ ቦታዎችን እና ቅርሶችን የማልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መኾኑን የምሥራቅ ጎጃም ዞን ባሕልና ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ።

0
106

ደብረ ማርቆስ: ሚያዚያ 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የምሥራቅ ጎጃም ዞን በርካታ ሰው ሠራሽ እና የተፈጥሮ መሥሕብ ሃብቶች ያሉት አካባቢ ነው። መርጡ ለማርያም የሚገኘው የአብርሐ ወአጽብሐ ግንብ፣ ደብረወርቅ ማርያም፣ ባሕረ ጊዮርጊስ፣ ዲማ እና ሌሎችም የመሥሕብ ሃብቶች ለአብነት ተጠቃሽ ናቸው።

በዞኑ የሚገኙ የመሥሕብ ሃብቶችን በማልማት የገቢ ምንጭ እንዲኾኑ የመሠረተ ልማት ማሟላት እና ቅርሶችን የመጠገን ሥራ እየተከናወነ መኾኑን የዞኑ ባሕል እና ቱሪዝም መምሪያ ኀላፊ ብርቄ ይዘንጋው ገልጸዋል።

በክልሉ ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ ድጋፍ እና በማኅበረሰብ ተሳትፎ በተገኘ ከ3 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ በኾነ ወጭ ሙዚየም እየተገነባ ስለመኾኑም ኀላፊዋ ተናግረዋል።

ሃይማኖታዊ እና ሕዝብ የሚታደምባቸውን በዓላት መነሻ በማድረግ የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን ለማነቃቃት እየተሠራም ነውም ብለዋል።

ለሀገር ውስጥ እና ለውጭም ጎብኝዎች ማረፊያ የሚሆኑ ሆቴሎችን እና ሎጂዎችን ለመገንባት በኢንቨስትመንት ዘርፉ ከባለሃብቶች ጋር እየተሠራ ስለመሆኑ ገልጸዋል።

ቅርሶች ተጠብቀው ከትውልድ ትውልድ እንዲተላለፉ እንክብካቤ ከማድረግ ባሻገር መዝግቦ እና ሰንዶ ለመያዝ እየተሠራ መሆኑንም ተናግረዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here