“የላሊበላን ውቅር አብያተክርስቲያናት ታሪክ እና ይዘት ጠብቆ ለትውልድ ለማሻገር እየተሠራ ነው ” ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)

0
99

ወልድያ: ግንቦት 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የርእሰ መሥተዳድሩ የአደረጃጀት አማካሪ ፍስሀ ደሳለኝ፣ የሰሜን ወሎ ዞን አሥተዳዳሪ አራጌ ይመር እና ሌሎች የክልል እና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች የላሊበላ ዘላቂ ልማት ኘሮጀክት አፈጻጸምን ጎብኝተዋል

የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) በብዝኅ ኢኮኖሚ ዕይታ የቱሪዝም ሀብቶችን እና መዳረሻዎችን ማልማት እና ከጉዳት በመጠበቅ ለጎብኚዎች ክፍት በማድረግ የቱሪዝም ገቢን ማሳደግ የመንግሥት መርህ ነው ብለዋል። ለዚህም በአማራ ክልል እየተሠሩ ያሉ የላሊበላ ዘላቂ ልማት ኘሮጀክት፣ የጎርጎራ ኢኮ ቱሪዝም ልማት፣ የፋሲል ቤተመንግሥት እድሳት እና የሎጎ ሐይቅ ገበታ ለሀገር ኘሮጀክት ተጠቃሽ ናቸው።

የላሊበላ ዘላቂ ልማት ኘሮጀክት የውቅር አብያተ ክርስቲያናት እድሳት እና ጥበቃ ከፈረንሳይ መንግሥት ጋር በመተባበር እየተሠራ መኾኑንም አስገንዝበዋል። የከባድ ጥገና እና የሽፋን ቅየራ ሥራ ጥንቃቄ የሚሻ በመኾኑ ተከታታይ ጥናት እየተሠራ ነው ብለዋል። በዚህም የላሊበላን ውቅር አብያተክርስቲያናት ታሪክ እና ይዘት ጠብቆ ለትውልድ ለማሻገር እየተሠራ መኾኑን ነው የገለጹት።

ትውልዱ የአባቶቹን አሻራ ጠብቆ የራሱንም አሻራ ለመጭው ትውልድ እያስቀመጠ ለመሄድ የሚያስችል ኘሮጀክት እንደኾነም ጠቁመዋል። የዘላቂ ልማት ሥራዎች አፈጻጸም አስደሳች መኾኑንም ተናግረዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here