ቡሄ እና የነገሥታቱ ልደት የተጣመሩበት ድምቀት።

0
39
ደብረታቦር፡ ነሐሴ 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የዓለምን ሚዛን ያስተካከሉ፣ የአስተሳሰብ ሊቆች፣ የጦር መሃንዲሶች፣ በብልሃት የተካኑ እየተባሉ በትውልድ ቅብብሎሽ ይሞካሻሉ፤ በአንድ ቀን የተወለዱት ጥንዶች ዳግማዊ አጼ ምኒልክ እና እቴጌ ጣይቱ።
የውልደት ቀናቸው ደግሞ ነሐሴ 12 ቀን ነው። ባል እና ሚስት ከአንድ ወንዝ ይቀዳሉ ይሉት ኢትዮጵያዊ ብሂልም በተግባር የተገለጠበት ዕለት ነው።ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አጼ ምኒልክ ነሐሴ 12/1836 ዓ.ም ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ እቴጌ ጣይቱ ደግሞ ነሐሴ 12/1832 ዓ.ም ነው የተወለዱት። የኢትዮጵያን ስም በከፍታ ላይ ያስቀመጡ፣ በዓለም ታሪክ ጥቁሮች ለመጀመረከያ ጊዜ ነጮችን እንደሚያሸንፉ በተግባር ያሳዩ የጦር መሃንዲሶች፣ በቴክኖሎጅ፣ በፖሊቲካ እና በኢኮኖሚ ጉዳዮች አዕምሯቸው ፈጥኖ የበራ እና ለኢትዮጵያም ያበራ ድንቅ ጥንዶች ናቸው።
የንጉሡ እና የንግሥቲቱ ልደትም በንግሥቲቱ የትውልድ አካባቢ ደብረታቦር ከተማ በድምቀት ተከብሯል። በእቴጌ ጣይቱ አደባባይ በተከበረው የልደት በዓላቸው ላይ የአማራ ክልል ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ ኀላፊ መልካሙ ፀጋየ፣ የደብረታቦር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ደሴ መኮንን፣ የክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ የከተማዋ መሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል። በበዓሉ ንጉሡን እና ንግሥቷን የሚዘክሩ የኪነ ጥበብ ሥራዎች ቀርበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here