ሻደይ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር ዝግጅት ተደርጓል።

0
35
ሰቆጣ: ነሐሴ 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሻደይ በዓል ሃይማኖታዊ መሠረት ያለው የልጃገረዶቸ በዓል ነው።
ይህንን በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓት መሠረት በሰቆጣ ከተማ ደብረ ፀሐይ ወይብላ ቅድስት ማርያም ካቴድራል በድምቀት ለማክበር መዘጋጀታቸውን የካቴድራሉ አሥተዳዳሪ መልአከ ፀሐይ ብርሃነ ሕይወት እንግዳ ገልጸዋል። የሻደይ በዓል በሦስት የቤተ ክርስቲያኗ ታሪክ መነሻነት የሚከበር እንደኾነ መልአከ ፀሐይ ተናግረዋል። ቀዳሚው በኦሪት ዘፍጥረት ላይ የሚገኘ የድኅነት፣ የደስታ፣ የነጻ መውጣት ምሳሌ ከኾነው የውኃ ሙላት የመዳን ምሳሌ እንደኾነ ገልጸዋል።
ይሄውም እርግቧ የለመለመ ቅጠል በማምጣት የውኃ ሙላቱ መጉደሉን በመግለጿ ኖኅ ከነልጆቹ እግዚአብሔርን አመስግኗልና። ዛሬም ልጃገረዶች የደስታ፣ የድኅነት፣ የነጻነት ምሳሌ የኾነውን የሻደይን ቅጠል ይዘው ይዘምራሉ ብለዋል። ሌላው መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክም በመጽሐፈ መሳፍንት የሚገኘው የዮፍታሔ ታሪክ ነው ይላሉ። ሦስተኛው ማሳያ የቤተ ክርስቲያኗ መነሻ የቅድስት ድንግል ማርያም እርገትን መላዕክት በክንፋቸው እያሸበሸቡ ሲያሳርጓት ቶማስ በደመና ሰቨኗን ወይም መግነዟን ተረክቦ ተመልሷልና የዚህን ምሳሌ በመውሰድ እንደመላዕክት ክንፍ ከወገባቸው ሻደዩን አስረው እመቤታችንን ያመሰግኑበታል ብለዋል። በዚህ ዓመትም በደብረ ፀሐይ ወይብላ ቅድስት ማርያም ካቴድራል በደናግላን ዘማሪያን በሻደይ ተውበው በዝማሬ እና በያሬዳዊ ወረብ ለማክበር መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
ዘጋቢ: ደጀን ታምሩ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here