ባሕርዳር ከተማ የተመቸ የአየር ሁኔታ እና ሳቢ ባሕል ያለባት ውብ ከተማ ናት።

0
64
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር በ’ጥርን በባሕር ዳር’ መርሐ ግብር የተለያዩ ኹነቶችን አዘጋጅቷል። የመርሐ ግብሩ አንድ አካል የኾነው የባሕል እና ኪነ ጥበባት ፌስቲቫል መካሄድ ጀምሯል።
በመክፈቻ መርሐ ግብሩ ላይም የውጭ ሀገር ጎብኝዎች ታድመዋል።
በፌስቲቫሉ ላይ እየታደሙ አሚኮ ያገኛቸው ኮስታድስ ዳፍኒስ ከግሪክ ወደ ኢትዮጵያ ለጉብኝት መምጣታቸውን ተናግረዋል። በፌስቲባሉ በተመለከቱት የባሕል ትዕይንት መደሰታቸውን ገልጸዋል።
በቆይታቸው በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎችን እየጎበኙ እንደኾነ ነው የጠቆሙት። የባሕር ዳር ከተማም የተመቸ የአየር ሁኔታ እና ሳቢ ባሕል ያለባት ውብ ከተማ ናት ብለዋል።
ውብ እና አስገራሚ ባሕል በማየታቸው የቆይታ ጊዜያቸውን አዝናኝ እንዳደረገላቸው ገልጸዋል።
ሌላኛው የውጭ ሀገር ጎብኝ ዲሜትሪዮስ አሌክሶፓሎስ ኢትዮጵያ ቆንጆ እና ውብ ባሕል ያለባት ሀገር ናት ብለዋል። በሄዱበት ሁሉ ቆንጆ ቆይታ እያደረጉ እና እየተዝናኑ እንደኾነም ገልጸዋል።
በተንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች አስደሳች እና ሳቢ የባሕል ብዝኃነት ያለ መኾኑን እንዳዩ
ጠቁመዋል።
ጉብኝታቸውን አጠናቅቀው ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ሌሎችም ኢትዮጵያን እንዲጎበኟት እንደሚጋብዙ ነው የተናገሩት።
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ ጋሻው እንዳለው በከተማዋ የውጭ ጎብኝዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል።
ባሕር ዳር ሰላሟ እየተረጋገጠ እና ለጎብኝዎች ምቹ እየኾነች በመምጣቷ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ጎብኝዎች ቁጥር እንዲጨምር ማድረጉን አመላክተዋል።
ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here