የግዮን አቡነ ዘርዓብሩክ በዓልን ለማክበር በቂ ዝግጅት ተደርጓል።

0
53
ፍኖተ ሰላም: ጥር 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በወርሐ ጥር በድምቀት ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት መካከል በሰከላ ወረዳ ጥር 13 ቀን የሚከበረው የግዮን አቡነ ዘርዓብሩክ በዓል አንዱ ነው።
በዓሉ በዚህ ዓመት ለስምንተኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ይከበራል። ይህ በዓል ሃይማኖታዊ ይዘቱን ጠብቆ እንዲከበር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የወረዳው ምክትል አሥተዳዳሪ ዓለማየሁ አዳነ ለአሚኮ ገልጸዋል።
በዓሉን ሊያከብሩ የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል እና በዓሉን አክብረው እንዲመለሱ የማረፊያ ቦታዎችን ማመቻቸት እና ሌሎች ሥራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።
ከኅብረተሰቡ እና ከሃይማኖት አባቶች ጋር በመቀናጀት በዓሉን በተገቢው መንገድ ለማክበር ሰፊ ርብርብ እየተደረገ መኾኑንም አንስተዋል።
የምዕራብ ጎጃም ዞን ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ መልኬ ያየህ በዞኑ ባለፉት ሁለት ዓመታት የነበረው የቱሪዝም ዘርፍ ከድባቴ እንዲወጣ እየተሠራ ነው ብለዋል።
ከወረዳው አሥተዳደር ጋር በመተባበር ግብረ ኃይል በማቋቋም ሰፊ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱንም ገልጸዋል።
የግዮን በዓልን ለቱሪዝም ዘርፉ መነቃቃት እንዲፈጥር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መኾኑንም አስረድተዋል።
በዓሉን በድምቀት ለማክበር የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል አስፈላጊ ዝግጅት በማድረግ በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙም አንስተዋል።
በዓሉን ለማክበር አስፈላጊ ዝግጅቶች በመደረጋቸው በሀገር ውስጥ እና በውጭ ለሚኖሩ ቱሪስቶች ወደ አካባቢው በመምጣት በዓሉን እንዲያከብሩ ጥሪ ቀርቧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here