“ጎንደር ግርማዋን ገለጠች፤ ካባዋን ደረበች”

0
42
ባሕር ዳር፡ ጥር 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) እናት ጎንደር ግርማዋን ገልጣለች፣ ካባዋን ደርባለች፤ ክብሯን አሳይታለች። እናት ጎንደር ዘውዷን ደፍታለች፤ ሰረገላዎቿን እንቀሳቅሳለች።
በመንበራቸው የነበሩ ታቦታት ወጥተዋል፤ ሊቃውንቱ እርግብ መስለው አጊጠዋል፤ ጎንደር በሕዝብ ተሞልታለች፤ ጎዳናዎቿ ከዋክብት በመሰሉ ምዕምናን ተጨንቀዋል።
ቅጽር እና ቅጽራቸው የገጠሙት የጎንደር አድባራት ደወላቸውን አስምተው ታቦታቱን አውጥተዋል። ጎንደር የሚያስደንቀውን ሥርዓት እየፈጸመች ነው።
ይህች ጥንታዊት እና ታሪካዊት ከተማ ለዓለም የሚያስደንቀውን ሥርዓት እያሳየች፤ የትናንቱን እያስታወሰች፤ የዛሬውን እየገለጠች ነው።
ጎንደር ጥምቀት በልዩ ሁኔታ ከሚከበወንባቸው ከተሞች መካከል ቀዳሚዋ ናት። ጥምቀት በጎንደር ብዙ ጎብኝዎች የሚታደሙበት ድንቅ ሃይማኖታዊ ሥርዓት ነው። ይህ ሥርዓት ከዛሬው የከተራ በዓል ጀምሮ መከወን ጀምሯል።
በታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here