በግሽ ዓባይ 8ኛው ሀገር አቀፍ የግዮን እና የአቡነ ዘርዓ ብሩክ ዓመታዊ በዓል እየተከበረ ነው።

0
34
ባሕር ዳር: ጥር 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ፣ የዓባይ ወንዝ መነሻ በኾነችው ግሽ ዓባይ ከተማ 8ኛው ሀገር አቀፍ የግዮን በዓል ከፃዲቁ አቡነ ዘርዓ ብሩክ ዓመታዊ የንግሥ በዓል ጋር በመቀናጀት እየተከበረ ነው የሚገኘው።
በዓሉ ካለፉት ሁለት ዓመታት በተለየ መልኩ እጅግ በርካታ እንግዶችን ያስተናገደ ሲኾን ከአራቱም መዓዘናት የመጡ አማኞች እና የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች የአካባቢውን የተቀደሰ በረከት ለመካፈል በሥፍራው ተገኝተዋል።
የዕለቱ ክብረ በዓል በሊቃውንቱ ዝማሬ፣ በሀገሬው ሆታ እና እልልታ የታጀበ ሲኾን አማኞች በባሕላዊ አልባሳት አሸብርቀው በመገኘት ለበዓሉ ልዩ ውበት ሰጥተውታል።
በዓባይ መነሻ ላይ የሚገኘው ይህ ሥፍራ በፃዲቁ አቡነ ዘርዓ ብሩክ ቡራኬ እና ቃል ኪዳን የተባረከ በመኾኑ አማኙ ለነፍስ ጽድቅ እና ለሥጋ ፈውስ በፀበሉ እየተጠመቁም ይገኛሉ።
የግዮን በዓል ከሃይማኖታዊ ይዘቱ ባሻገር የዓባይን ወንዝ ተፈጥሯዊ እና ታሪካዊ እሴት ለዓለም የሚያስተዋውቅ ታላቅ መድረክ መኾኑም ተመላክቷል።
በዓሉ በድምቀት የተጀመረ ሲኾን እንግዶችም በአካባቢው በረከት እና በተፈጥሮው አግራሞት ተመስጠው በዓሉን በማክበር ላይ ይገኛሉ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here