የቅዱስ መርቆሬዎስ በዓል የቱሪዝም ዘርፉን ሊያነቃቃ በሚችል አግባብ ለማክበር ዝግጅት ተደርጓል።

0
34
ደብረ ታቦር፡ ጥር 19/2018ዓ.ም (አሚኮ) ‎‎የቅዱስ መርቆሬዎስ በዓል በደቡብ ጎንደር ዞን አሥተዳደር፣ በእስቴ መካነ ኢየሱስ እና በደብረ ታቦር ከተማ ለማክበር ቅድመ ዝግጅቶች መከናወናቸውን የደቡብ ጎንደር ዞን አሥተዳደር አስታውቋል።
በዓሉ ማኅበረሰባዊ ትስስር ከመፍጠሩ በላይ የቱሪዝም ዘርፉን እንደሚያነቃቃ የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ ጥላሁን ደጀኔ ተናግረዋል ::
ታሪካዊ እና ሃይማኖታዊ ትውፊቶች ሳይበረዙ ለማስቀጠል በጋራ ሥራዎችን በመሥራት ትልቅ የቱሪዝም ሃብት እና መስህብ ለማድርግ ሰፊ ሥራዎች መሠራታቸውንም ተናግረዋል።
በዓሉን በዓለም አቀፍ የቅርስ ሃብቶች መዝገብ ውስጥ ለማስመዝገብም ትኩረት በመስጠት እየተሠራ ነው ብለዋል።
እርስ በእርስ የተዋደደ ማኅበረሰብ ለመገንባት ሃይማኖታዊ በዓላት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መኾናቸውንም ገልጸዋል።
የደቡብ ጎንደር ዞን አሥተዳደር ባሕል ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ ስሜነህ ደሳለኝ በዓሉን ለማክበር ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል።
ኀላፊው በዓሉ ሃይማኖታዊ፣ ታሪካዊ እና ባሕላዊ ይዘት ያላቸው የፈረስ ጉግስ፣ ባሕላዊ ዝግጅቶች እና ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች በድምቀት የሚከናወኑበት ነውም ብለዋል።
በዓሉን ለማክበር ለሚመጡ እንግዶች ምቹ ሁኔታዎች መፈጠራቸውን ጠቅሰው በእስቴ መካነ ኢየሱስ እና በደብረ ታቦር ከተማ የሚከበረውን የቅዱስ መርቆሬዎስ ዓመታዊ የንግሥ በዓል በጋራ ለማክበር ለእንግዶች ጥሪ አቅርበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here