ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በቅዱስ መርቆሬዎስ ዓመታዊ ክብረ በዓል ለመታደም ደብረ ታቦር ገብተዋል።

0
13
ባሕር ዳር: ጥር 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በቅዱስ መርቆሬዎስ ዓመታዊ ክብረ በዓል ለመታደም ደብረታቦር ከተማ ገብተዋል።
በበዓሉ ላይ ለመታደም ደብረታቦር የገቡት የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ናቸው። ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎቹ ወደ ታሪካዊቷ ደብረታቦር ከተማ ሲገቡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የቅዱስ መርቆሬዎስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በደብረ ታቦር ከተማ በድምቀት ይከበራል። በታሪካዊው አጅባር ሜዳ በሚከናወነው ዓመታዊ ክብረ በዓል ከሃይማኖታዊ ሥርዓቱ ባለፈ ባሕላዊ እና ታሪካዊ ክዋኔዎች ይፈጸሙበታል።
የፈረስ ጉግስ የበዓሉ ድምቀት ነው። በርካታ እንግዶችም ይህን አስደናቂ በዓል ለመታደም ወደ ደብረታቦር ያቀናሉ። ይህ በዓል ለአካባቢው የቱሪዝም መዳረሻ በመኾን የሚያገለግል አስደናቂ ነው።
ዘጋቢ:- ዳግማዊ ተሠራ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here