ባካሪ ሳኛ በጣና ዳር እየተገነባ የሚገኘውን የፈለገ ግዮን ሪዞርትን ጎብኝቷል።

0
13
ባሕር ዳር: ጥር 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የቀድሞው የአርሰናል እና የማንቸስተር ሲቲ ተጫዋቹ ባካሪ ሳኛ በባሕር ዳር ከተማ ጣና ዳር እየተገነባ የሚገኘውን የፈለገ ግዮን ሪዞርትን ጎብኝቷል።
ባካሪ ሳኛ የባሕር ዳር ስታድዬምን ከጎበኘ በኋላ ነው የፈለገ ግዮን ሪዞርትን የጎበኘው።
ባካሪ ሳኛ በጣና ዳርቻ ባየው ውበት መደሰቱን ገልጿል። ሥፍራው ማራኪ እና ውብ መኾኑንም ተናግሯል። ለመዝናኛ የሚመረጥ እና የተመቸ ሥፍራ መኾኑንም አንስቷል።
ሳኛ በኢትዮጵያ ቆይታው አስደናቂ ሥፍራዎችን ማየቱንም ተናግሯል። ኢትዮጵያ የታሪክ እና የባሕል ሃብታም፤ ምድረ ቀደምት ታላቅ ሀገር መኾኗንም ገልጿል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here