ባሕር ዳር: የካቲት 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የፈቂ አባስ መስጅድ በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በዱላ ቀበሌ ከሰንበቴ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ መስጅ ነው፡፡
መስጅዱ ሙሉ በሙሉ ከድንጋይ እና ከተመረጠ ልዩ አፈር የተሠራ ነው፡፡ ይህ መስጅድ ጥንታዊ ከሚባሉ መስጅዶች አንዱም ነው፡፡
በመስጅዱ የውስጥ ገጽታ ላይ በቁፋሮ የተገኘው የጽሑፍ መረጃ እንደሚያስረዳው የተሠራው በሂጅራ አቆጣጠር በ171 ነው፡፡
ከጥንታዊነቱም ጋር ያለው የኪነ ሕንጻ ጥበብ ቦታው ለተጨማሪ ጥናት የሚጋብዝ እንደኾነ ከአማራ ክልል ባሕል ቱሪዝም ቢሮ የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!