ሌላው ድንቅ ሀብት – ገነተ ማርያም

0
334

👉የገነተ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከላሊበላ ከተማ ወደ ወልዲያ በሚወስደው አማራጭ የጠጠር መንገድ 31 ኪሎ ሜትር ርቀት ትገኛለች፡፡
👉ቤተ ክርስቲያኗ በከፊል ውቅር ስትሆን በ1260ዎቹ በአጼ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት እንደተሠራች ይነገራል፡፡
👉የቤተ ክርስቲያኗ አብዛኛው ክፍል በጥንቃቄ ተፈልፍሎ ከቋጥኝ እና ገደል ነፃ ሆኖ ለብቻው የቆመ በመሆኑ ከላሊበላው ቤተ መድኃኒዓለም ጋር ያመሳስላታል፡፡
👉በዙሪያው የሚገኘው የተጠረበው ቋጥኝ ደግሞ እንደ አጥር የሚያገለግል ሲሆን በመግቢያው በር ግራ እና ቀኝ የመስቀል ቅርጽ ተቀርጾበታል፡፡
👉በሕንፃው ውስጥ ጥንታዊ የኢትዮጵያን ባሕላዊ የሥዕል አሳሳል ስልት የተከተሉ የግድግዳ እና ጨርቅ ላይ የቀለም ቅብና የገበታ ላይ ሥዕሎች ይገኛሉ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here