ታሪካዊው መንዳባ አቡነ ያሳይ አንድነት ገዳም

0
418

ባሕር ዳር: መጋቢት 4/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምዕራብ ደምቢያ ወረዳ የምትገኘው ጎርጎራ የጣና ሐይቅ ወደብ ከመሆኗ ባሻገር በደሴቶቿ እና በዳርቻዋ በርካታ ታሪካዊ ገዳማት ይገኛሉ።

ከእነዚህም ውስጥ ደብረ ሲና ማርያም፣ መንዳባ መድኃኒዓለም፣ ብርጊዳ ማርያም፣ ገሊላ ኢየሱስ፣ አንጋራ ተክለሃይማኖት፣ እጅ በራ ማርያም ይገኙበታል፡፡

እነዚህ ገዳማት አንዳንዶቹ ከ700 ዓመት ዕድሜ በላይ ያላቸው ሲኾኑ በውስጣቸው ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተሰባሰቡ ውድ የታሪክ ቅርሶች እና የመካከለኛው ዘመን የሀገሪቱ ነገሥታትን አፅም የያዙ ናቸው።

ይህ ብቻ ሳይሆን በጎርጎራ እና አካባቢዋ የአጼ ሱስንዮስ ቤተ መንግሥት ፍርስራሽ እና ሌሎችም የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች ያሉበት አካባቢ ነው።በጎርጎራ ከሚገኙት ጥንታዊ እና ታሪካዊ ገዳማት አንዱ ማን እንደ አባ አቡነ ያሳይ አንድነት ገዳም ነው።

መንዳባ አቡነ ያሳይ መድኃኒዓለም አንድነት ገዳም ከጎርጎራ ከተማ በስተምዕራብ በኩል 5 ኪ.ሜ ርቀት ከተንጣለለው የጣና ሐይቅ ዳርቻ ላይ ይገኛል።ገዳሙ በ1326 ዓ.ም በቀዳማዊ አምደጽዮን ልጅ በፃዲቁ አቡነ ያሳይ እንደተመሠረተ ይነገራል ሲል የማዕከላዊ ጎንደር የመንግሥት ኮሙንኬሽን አስነብቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here