ሳላይሽ የዳግማዊ ምኒልክ የጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት

0
258

👉የሚገኘው ኮረማሽ ከተማ ከባሕር ዳር 679 ኪሎ ሜትር፣ ከአዲስ አበባ 88 ኪሎ ሜትር እንዲሁም ከደብረ ብርሃን 68 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው።
👉ቦታው በ1890 ዓ.ም ከዓድዋ ድል በኋላ ለጦር መሣሪያ ማከማቻነት ተብሎ እንደተሠራ ይነገራል።
👉የቦታው የተፈጥሮ አቀማመጥ ቀልብን የሚስብ፣ ለጦርነት ስትራቴጅ ከፍታ ምቹ እና ሁሉንም መቆጣጠር የሚያስችል በመሆኑ “እስካሁን ሳላይሽ ቆየሁ” በማለት ስያሜው እንደተሰጠው ይነገራል።
👉ቤቶቹ በእንቁላል ቅርጽ ከድንጋይ፣ ከእንጨት እና ከጭቃ የተሠሩ ሲሆን በዙሪያቸው 14 ረድፎች (ብሎክ) ነበራቸው።
👉ከግምጃ ቤቱ በስተጀርባ ጠባዝላ የሚባል ቦታ አለ፤ ከዚህ ቦታ ላይ ሆኖ እጅግ ድንቅ የሆነ መልከዓምድራዊ አቀማመጥ ያለው ቦታ ይታያል።
👉በአሁኑ ሰዓት ተጠብቆ ለጉብኝት ክፍት ሆኗል።
ምንጭ፡- አማራ ድንቅ ምድር መጽሐፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here