ሞገዳ ግንብ

0
283

ባሕር ዳር: መጋቢት 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሞገዳ ግንብ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በአለፋ ወረዳ ከሚገኙ ጥንታዊ እና ሰው ሠራሽ የመስህብ ሃብቶች አንዱ ነው፡፡
ይህ ግንብ ከሻውራ ከተማ በ22 ኪሎ ሜትር ርቀት በሰሜን አቅጣጫ በቸባ ሞገዳ ቀበሌ ውሰጥ ይገኛል፡፡

ግንቡ በአፄ ፋሲል ዘመነ መንግሥት በ1634 ዓ.ም እንደተሠራ ይነገራል፡፡ የሞገዳ ግንብ በአፄ ፋሲል ቤተ መንግሥት ካሉት ሕንፃዎች ውስጥ ከአብዛኛዎቹ ጋር የሚመሳሰል ሲኾን በይበልጥ ግን ከአፄ አዲያም ሰገድ ዳዊት ደባል ሕንፃ ጋር እንደሚመሳሰል የተመለከተው ሰው ልብ ይላል፡፡

ምንም እንኳን ቅርሱ አሁን ያለበት ደረጃ ሳቢ፣ ማራኪ እና ጥንታዊ ይዘቱን የጠበቀ ቢኾንም በተፈጥሮ እና ሰው ሠራሽ አደጋዎች እየፈራረሰ ቅርስነቱን እና መስህብነቱን እያጣ ይገኛል ሲል ማዕከላዊ ጎንደር ኮሙንኬሽን ዘግቧል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here