ቀደምቷ የጉምሩክ መስራች ከተማ – አልዩ አምባ

0
293

👉ከአዲስ አበባ 187 ኪሎ ሜትር፣ ከደብረ ብርሃን 57 ኪሎ ሜትር እንዲሁም ከአንኮበር ወረዳ ዋና ከተማ ጎረቤላ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች።
👉የስምጥ ሸለቆ አካል ነች።
👉የተመሠረተችው በ1266 ዓ.ም እንደሆነ ይነገራል።
👉የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ የንግድ ማዕከል እንደነበረች ትጠቀሳለች።
👉አልዩ አምባ የሚለውን ስያሜ ያገኘችው “አልየ” ከተባለ የአካባቢው ነጋዴ ሥም በመነሳት እንደሆነ ይወሳል።
👉ከተማዋ ለረጅም ርቀት ንግድ ምቹ በመኾኗ በወቅቱ እስከ ዘይላ ወደብ ድረስ ተዘርግቶ የነበረው የሲራራ ንግድ ማዕከል ነበረች።
👉በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን የቀረጥ መሥሪያ ቤት ተከፍቶ የጉምሩክ ጽሕፈት ቤት ሥራውን ጀምሮባታል።
👉በዘይላ ወደብ የንግድ መስመር በኩል ወደ ሀገራችን በሚገቡ የንግድ ዕቃዎች ላይ የቀረጥ ክፍያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጀመረባት እና የኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ የጉሙሩክ ከተማ ነች።
👉ሞቃታማ እና ተስማሚ የአየር ንብረት የታደለች ናት።
👉አትክልት እና ፍራፍሬ በብዛት ይገኙባታል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here