👉ዳግማዊ ቴዎድሮስ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብለው የነገሡባት ታሪካዊ ደብር ናት።
👉በወርቅ ቅብ ጉልላት አጊጣ የተሠራችው ደረስጌ ማርያም ከደጃች ውቤ እና ከዳግማዊ ቴዎድሮስ ጋር የሚገናኙ በርካታ ቅርሶችን የያዘች ቤተ ክርስቲያን ናት።
👉የወርቅ እና የብር ቅብ ከበሮዎች፣ የነገሥታት ዘውዶች፣ ካባዎች፣ የተለያዩ የወርቅ እና ብር መስቀሎች፣ የብራና መጻሕፍት እና ሌሎች ቅርሶች በቤተ ክርስቲያኗ እቃ ቤት ይገኛሉ።
👉የቤተ ክርስቲያኗ ዙሪያ በእድሜ ጠገብ የጽድ ዛፎች የተከበበ ነው።
👉የአጼ ቴዎድሮስ ሁለተኛ ሕጋዊ ባለቤት እና የልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስ እናት የእቴጌ ጥሩወርቅ የትውልድ ቦታ በመሆኗ ታሪካዊ ፋይዳዋ ከፍተኛ ነው።
👉ደረስጌ በሰሜን ጎንደር ዞን ጃንአሞራ ወረዳ ከጎንደር ከተማ 150 ኪሎ ሜትር ከደባርቅ ከተማ 49 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች።
ምንጭ:- አማራ ድንቅ ምድር መጽሐፍ