የዘንድሮውን የጥምቀት በዓል የጎንደርን ታሪክ ፣ባህል፣ እምነት እና ፀጋዎችን ለማሳወቅ በሚያስችል መልኩ ለማክበር ዝግጅት መጀመሩን ከተማ አሥተዳደሩ አስታወቀ። 

0
202

ባሕር ዳር፡ ኅዳር 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጎንደር የጥምቀት በዓልን “ጥምቀትን በጎንደር” በሚል መሪ ቃል በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት መደረጉን ከተማ አሥተዳደሩ ገልጿል።

 

የ2016 ዓ.ም የጥምቀት በዓልን በተመለከተ ከተማ አሥተዳደሩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ዛሬ ውይይት አድርጓል።

 

በውይይት መድረኩ የተገኙት የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ባዩህ አቡሀይ፤ የጥምቀት በዓል ባለፉት ዓመታት የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ከኢትዮጵያ ቅርስ አሥተዳደር አገልግሎት ድርጅት ጋራ በጋራ በሠራው ከፍተኛ ሥራ በዓለም ቅርፅነት በዩኒስኮ እንዲመዘገብ የተደረገ ሀገራዊ በዓል ነው፡፡

 

ከአካባቢዊ ፋይዳ ወጥቶ ለዓለም ሕዝቦች ያለው ፋይዳ ጉልህ መሆኑ ታመኖበት የተመዘገበ በመሆኑ ይህ በዓል ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል ብለዋል፡፡

 

ከንቲባው አክለውም የ2016 ዓ.ም የጥምቀት በዓልን በድምቀት ለማክበር አንድ አብይ ኮሚቴና 8 ንዑሳን ኮሚቴዎች ተጀራጅተዋል። ኮሚቴዎቹ ዕቅድ አቅደው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ ብለዋል።

 

የጎንደር የ2016 ዓ.ም የጥምቀት በዓልን ስናከብርም ትልቁ ግባችን የከተማዋን ምስል ፣ ኢኮኖሚና ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ የሚያስችል ሁኔታዎችን ይይዛል፡፡ የጎንደርን ታሪክ ፣ባሕል፣ እምነት አጠቃላይ ያሏትን ፀጋዎችን ለማሳወቅ ያስችላል፡፡

 

የጎንደር ከተማ አሥተዳደር የ2016 ዓ.ም የጥምቀት በዓልን “ጥምቀትን በጎንደር” በሚል መሪ ቃል በደማቅ ሁኔታ ለማክበር እየተሠራ መሆኑን የከተማ አሥተዳደሩ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

 

በበዓሉ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የሀገር ውስጥና የውጭ ጎብኝዎች እንዲታደሙ ጎንደር ጥሪዋን ታቀርባለች።

 

ጥምቀትን በጎንደር አይረሴ የመልካም ትዝታ ስንቅ ነው ያለው ከተማ አሥተዳደሩ “ጎንደር ከእንግዶቿ ጋር በጥምቀት እንደወትሮዉ ሁሉ ዘንድሮም ትደምቃለችና ሁላችሁም በጎንደር ጥምቀት ከወዲሁ ተጠርታችኋል” ሲል ግብዣውን በይፋ አቅርቧል፡፡

 

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here