የጣና ዳር ፈርጧ ደልጊ ከተማ

0
377

ባሕር ዳር: ግንቦት 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የጣና ዳር ፈርጧ ደልጊ ከተማ በሚያስደንቅ መልክዓምድራዊ አቀማመጧ፣ የዓሣ ምግብ እና ብዙ የሚቃኙ ቦታዎች፥ ባሕል፣ ታሪክና ወግ አቅፋ የያዘች ድንቅ ምድር ናት። እጅግ በጣም ጥሩ የኾነ የቅመማ ቅመም ሰብሎች የሚመረቱባትና የጣና ሐይቅን ተንተርሳ የተመሠረተችው ደልጊ ዓመቱን ሙሉ በለምለም እርሻዎቿ ትታወቃለች።

አካባቢው በታሪክም ይታወቃል፤ ጥንታዊ ቦታዎችን እና የተፈጥሮ የውበት ቦታዎችን ማሰስ ለሚወዱ ተጓዦች መዳረሻ መኾን የምትችል ከተማ ናት። ከማዕከላዊ ጎንደር ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው ደልጊና አካባቢዋ ታንኳ እና ዓሣ ማጥመድ የመሳሰሉት እንቅስቃሴዎቿ ለማራኪ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታ ተመራጭ ያደርጋታል። ፀጥ ባለ የሐይቅ ዳርቻ ስር የተመሠረተችው ደልጊ ከተማ እጅግ አስደናቂ የሆነ መልክዓምድር ባለቤት ናት።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here