👉በንጉሥ ሚካኤል ልጅ ወ/ሮ ስኂን ሚካኤል የ25 ሺህ ማርትሬዛ ድጋፍ ሐምሌ 7/1922 ዓ.ም ተቋቋመ
👉በደሴ ከተማ ሳላይሽ አካባቢ ይገኛል
👉በ1939 ዓ.ም የመጀመሪያ አጠቃላይ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሆነ
👉በወሎ ጠቅላይ ግዛት የመጀመሪያው የመንግሥት ትምህርት ቤት ነበር
👉በ1950 ዓ.ም ተጨማሪ ክፍል በመገንባት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሆነ
👉ግርማዊት እቴጌ መነን 60 ሺህ ብር ወጭ አድርገው የእጅ ሥራ ትምህርት ቤት አሠርተው በ1953 ዓ.ም አስረከቡ
👉በአሁኑ ሰዓት የፖሊ ቴክኒክ አገልግሎት በመስጠት ላይ ነው
ምንጭ፡- የደቡብ ወሎ ኮሙዩኒኬሽን