👉ደብረ ታቦር ከተማ በ1327 ዓ.ም በአጼ ሰይፈአርዕድ ተመሰረተች
👉ለበርካታ ዓመታት የማዕከላዊ መንግሥት መቀመጫ ነበረች
👉በዘመነ መሳፍንት ወቅት ለመሳፍንቶች ተመራጭ ከተማ እንደነበረች ታሪክ ያስረዳል
👉ከዘመነ መሳፍንት መክሰም በኋላም ታላቁ ንጉሥ አጼ ቴዎድሮስ በዋና ከተማነት መርጠዋታል
👉የመጀመሪያው የብረት ኢንዱስትሪ የተገነባበት ቦታ መገኛም ናት
👉የቄንጠኛ ፈረሰኞች ሽምጥ ግልቢያ እና ጉግሥ የከተማዋ አንዱ መገለጫ ባሕል ነው
👉የአጼ ሰርጸ ድንግል፣ የአጼ ሱስንዮስ፣ የአጼ ቴዎድሮስ፣ የአጼ ዮሐንስ የቤተ መንግሥት አሻራዎቻቸው አሁንም ይገኛሉ
👉ብርሃን ዘ-ኢትዮጵያ እቴጌ ጣይቱ የተወለዱት እና ለሀገር ቁምነገርን የቀሰሙበት ከተማ ናት
👉የአሸንድዬና የቡሔ በዓላት ሌሎች ውብ ባሕላዊ ድምቀቶቿ ናቸው
👉በኢትዮጵያ ብቸኛው የተክሌ አቋቋም የዜማ ማስመስከሪያ በከተማዋ ይገኛል
ምንጭ:- ደብረ ታቦር ኮሙኒኬሽን