👉የጮቄ ተራራ ሰፊ ተፋሰስ የሚሸፍን ነው
👉ሰባት የሚኾኑ የምሥራቅ ጎጃም እና ምዕራብ ጎጃም ወረዳዎችን ያዋስናል
👉ከነዚህ ወረዳዎች መካከል በምዕራብ ጎጃም የሚገኘው የደጋ ዳሞት ወረዳ አንዱ ነው
👉ደጋ ዳሞት እ.ኤ.አ በ2022 የዓለም ምርጥ የቱሪዝም መንደር (Best Tourism Village) አሸናፊ የኾነው የሙሉ ኢኮ ሎጅ መገኛ ነው
👉በገነት የተፈጥሮ ሀብት ቱሪዝም ኅብረት ሥራ ማኅበር የሚተዳደረው ሙሉ ኢኮ ሎጅ ማኅበረሰብ ተኮር ቱሪዝምን በማስፋፋት እና አካባቢን በመጠበቅ በመጀመሪያው የድንቅ ምድር የእውቅና እና ሽልማት መርሐ-ግብርም አሸናፊ የኾነ ድንቅ ሎጅ ነው