ባሕር ዳር: ጻጉሜን 03/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ቲፋሻ ፏፏቴ በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ከማክሰኞ ገበያ ከተማ በቅርብ ርቀት ይገኛል።
አካባቢው ምጭዊ በመባል የሚታወቅ ሲሆን የጠገዴ ስምንቱ ማይቤት የተመሰረተበት ታሪካዊ ስፍራ ነው።
ቆላማና ወይናደጋ የአየር ንብረት ያለው ይህ አካባቢ ለዓይን የሚማርክ ተራራማ፣ ሸለቆና ሜዳማ መልክዓምድራዊ ባለቤት ነው።
አካባቢው በተለይም በዚህ ወቅት ውበቱ የበለጠ የሚገለጥበት በመኾኑ ሊጎበኙት የሚገባ ድንቅ የወልቃይት መልክ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!