ከደሴ ከተማ 37 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው የሳልሙኔ ከተማ ደቡባዊ አቅጣጫ 2ዐ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል
የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል (መውሊድ) ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገራችን የተከበረበት ቦታ እንደኾነ ይታመናል
መስጅዱ በ1756 ዓ.ም በታላቁ የእስልምና ምሁር ሐጅ ሰይድ ሙጃሂድ የተቆረቆረ ነው
የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል (መውሊድ) በድምቀት እና ባማረ መልኩ ከሚከበርባቸው የሀገራችን አካባቢዎች ዋናው ነው
ምንጭ:- አማራ ድንቅ ምድር መጽሐፍ