የምሥራቅ አፍሪካ የውኃ ማማ ነው ከባሕር ወለል በላይ 4ሺህ 88 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል ጠቅላላ ስፋቱ 53 ሺህ 558 ሄክታር በላይ እንደሚደርስ ጥናቶች ያመለክታሉ በምሥራቅ ጎጃም በ8 ወረዳዎች እና በምዕራብ ጎጃም ዞን በ1 ወረዳ ክልል ውስጥ ይገኛል::
እነማይ እና እናርጅ እናውጋ፣ ሰዴ፣ ቢቡኝ፣ ማቻከል፣ ስናን እንዲሁም ደባይ ጥላት ግን ወረዳዎች ያዋስናል ከፍተኛ ቅዝቃዜ አለው፤ በተለይም በክረምት ወቅት ከሳምንት በላይ በበረዶ ይሸፈናል፡፡
ነገር ግን አሁን አሁን የበረዶ ግግር እየቀነሰ የመጣበት ኹኔታ ይታያል 23 ትላልቅ ወንዞችና 273 ትናንሽ የዓባይ ገባሮች ከስሩ የሚፈልቁበት የውኃ ጋን ነው የመሬት አቀማመጥ 86 ከመቶ ተራራማ፣ 1 ነጥብ 5 ከመቶ ሸለቋማ እና 12 ነጥብ 5 ከመቶ ሜዳማ ነው ጮቄ በጣም ሰፊ ከመኾኑም የተነሳ ገና ብዙ ያልታወቁ ዋሻዎች፣ ጥንታዊ መኖሪያዎችና ያልተዳሰሱ አስደሳች የተፈጥሮ መስኅቦች አሉት የጮቄ የላይኛው አካል በአብዛኛው ሜዳማ ኾኖ በጅባራ፣ ግምይና አሸንግድየ ተክሎች የተሸፈነ ነው
ጠቅላላ ስፋቱም ወደ 53 ሺህ 558 ሄክታር እንደሚደርስ በአካባቢው የተደረጉ ጥናቶች ያመለክታሉ ይህ ቦታ ለቱሪስት ማረፊያነት ማገልገል የሚችል ሲኾን የአካባቢውን ገፅታ ለመመል ከት የሚያስችል ከፍተኛ ቦታ ነው፡፡ የጮቄ ተራራ ልዩ ውበትና ተፈጥሯዊ ፀጋ የተላበሰ ነው
የጮቄ ማኅበረሰብ ጥብቅ ስፍራ ተቋቁሞ እንዲጠበቅና እንዲለማ 6ሺህ 24 ሄክታር መሬት ተከልሎ ማኅበረሰቡ እንዲጠቀምበት ለማድረግ ጽሕፈት ቤት ተቋቁሞለታል
ምንጭ፦ የአብክመ አካባቢና ደን ጥበቃ ባለሥልጣን