ባሕር ዳር: ኅዳር 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሙሉዓለም የባሕል ማዕከል የኪነ ጥበብ ልዑክ በሩሲያ ካዛን ከተማ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ሲያስተዋውቅ አምሽቷል። የአማራ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ መሪዎች እና ሙሉዓለም የባሕል ማዕከል የኪነ ጥበብ ቡድን በሩሲያ ካዛን ከተማ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል ላይ ኢትዮጵያን ወክለው መገኘታቸው ይታወሳል።
ወደስፍራው ያቀናው የሙሉዓለም የባሕል ማዕከል የኪነ ጥበብ ልዑክ በዓለም አቀፉ መድረክ ላይ የተለያዩ የኪነ ጥበብ ሥራዎቹን ለተመልካች አቅርቧል። ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትንም በዓለም አደባባይ ሲያስተዋውቁ አምሽተዋል።
የኪነ ጥበብ ልዑኩ ባቀረባቸው ኢትዮጵያዊ የጥበብ ሥራዎች አድናቆት እና ምስጋና ተችሮታል። ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የዘርፉ መሪዎች እና ባለሙያዎች ጋርም ትውውቅ የተደረገበት መድረክ እንደነበር የአማራ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ መረጃ አመላክቷል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!