ጥንታዊው የቅዱስ ገላውዲዎስ ቤተክርስቲያን

0
169

ደብረ ታቦር: ታኅሣሥ 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጥንቱን የሚናገር፣ ያለፈውን የሚዘክር፣ ታሪክና ሃይማኖትን የሚያስተምር ታላቅ ሥፍራ ነው። በደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ ይገኛል ጥንታዊው ቤተክርስቲያን ቅዱስ ገላውዲዎስ። ይህ ጥንታዊ ቤተክርስቲያን የተመሠረተው በንጉስ ገላውዲዎስ አማካኝነት በ1543 ዓ.ም እንደኾነ ይነገራል።

በቤተክርስትያኑ ውስጥ የአጼ ቴዎድሮስ ምንጣፍ፣ የንግሥት ዘውዲቱ የወርቅ መርገፍ ምንጣፍ ፣ መከዳ፣ ትራስ፣ የአጼ ገላውዲዎስ ቀንደ መለከት፣ ፈረስ ላይ ሲቀመጡ የሚለብሱት ሰናፊ እና ሌሎች መንፈሳዊ እና ታሪካዊ ቅርሶች ይገኙበታል፡፡

አበው እንደሚሉት ንጉሥ ገላውዲዎስ በነበሩበት ዘመን አብራ የመጣች ንብ እስካሁን ድረስ በቤተክርስቲያኑ በር ላይ ትገኛለች፡፡ ይህች ንብ የምትሰጠውን ትንሽ ማርም አማኞች ለመድኃኒትነት ይጠቀሙበታል። የጎብኚዎችን ቀልብ የሚስብ፣ የቀደመውን ታሪክ የሚዘክር የሀገር ሀብት ነው።

ከደቡብ ጎንደር ዞን ባሕል እና ቱሪዝም መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው አሁን ላይ የዚህ ጥንታዊ እና ታሪካዊ ቤተክርስቲያን አጥር ቅርስነቱን ሳይለቅ በአማራ ክልል ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ እና በኅብረተስቡ ተሳትፎ እየተጠገነ ነው።

በሀገር ውስጥም ኾነ ከሀገር ውጭ ያሉ አማኞች፣ መንግሥታዊ የኾኑ እና መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶች እገዛ እንዲያደርጉም ተጠይቋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here