“ጥርን በባሕር ዳር” በድምቀት ለማክበር ዝግጅት እያደረገ መኾኑን የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር አስታወቀ።

0
237

ባሕር ዳር: ጥር 2/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ባሕል እና ቱሪዝም መምሪያ “ጥርን በባሕር ዳር” በድምቀት ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ስለመኾኑ ተገልጿል። ባሕር ዳር ከተማ ብዙ ጸጋ ያላት እና ዓመቱን ሙሉ የቱሪስት መዳረሻ የኾነች ከተማ ናት።

ከተማዋን በተለይም የሀገር ውስጥም ኾነ የውጭ ሀገር ቱሪስቶች ፕሮግራም ይዘው እንዲጎበኟት ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ ተገልጿል። ከተማዋ ከዛሬ ስምንት ዓመት በፊት ጀምሮ ሃይማኖታዊም ኾነ ባሕላዊ ሁነቶች በብዛት የሚከበርበት ወር ተመርጦ “ጥርን በባሕ ርዳ “በሚል ጥር ወርን በተለያዩ ዝግጅቶች ማክበር እንደ ጀመረች የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የባሕል እና ቱሪዝም መምሪያ ኀላፊ ጋሻው እንዳለው ተናግረዋል፡፡

ለእንግዶች በሚመች መልኩ የጥር ወር ማድመቂያ መርሐ ግብሮች ሲዘጋጁ መቆየታቸውንም ነው ያስረዱት፡፡ በዚህም ከጥር 01/2017 ዓ.ም ጀምሮ አስከ ጥር 30/2017 ድረስ የቱሪስቶችን ቀልብ የሚስቡ እና የከተማዋን ገጽታ የሚገነቡ የተለያዩ ባሕላዊ እና ሃይማኖታዊ ሁነቶች እንደሚከናዎኑም አስገንዝበዋል፡፡

በሂደቱም የንግድ ባዛር እና ኤግዚቢሽን፣ የኪነ-ጥበብ በዓል እና የኪነ-ጥበብ ፌስቲባል፣ የከተማዋ የቱሪዝም መዳረሻ መሠረተ ልማቶች ጉብኝት፣ የብስክሌት ሽርሽር እና ባሕር ዳርን የማስዋብ ዘመቻ በጥር ወር እንደሚከናዎኑም ነው ያብራሩት፡፡ ከከተማዋ ወጣቶች ጋር በመተባበርም ለከተራ በዓል ከተማዋን የማድመቅ እና ለበዓሉ ዝግጁ የማድረግ ሥራ እንደሚሠራም ጠቁመዋል፡፡

በከተማዋ ወሩን ሙሉ የተለያዩ ሁነቶችን በመጠቀም ከተማዋን የቱሪዝም መዳረሻ የማድረግ ሥራ እንደሚሠራ እና በመጨረሻም በሥራው ላይ ለተሳተፉ አካላት ዕውቅና የመስጠት ሥነ ሥርዓት በማካሄድ እንደሚጠቃለል ኀላፊው አሳውቀዋል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here