ባሕር ዳር: ጥር 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ኢራንቡቲ 44 ታቦታት ወደ ባሕረ ጥምቀት የሚወርዱባት ድንቅ ምድር ናት፡፡ ጥምቀት በኢራንቡቲ መከበር የጀመረው ከ600 ዓመታት በፊት በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደኾነ ይነገራል።
ከቪዚት አማራ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ዳግማዊ ዮርዳኖስ እየተባለ በሚጠረው የሸንኮራ ወንዝ የሚከበረው የጥምቀት በዓል ልዩ ድምቀት አለው።
ኢራንቡቲ ጥምቀት በድምቀት ከሚከበርባቸው አካባቢዎች መካከል ከቀዳሚዎቹ ናት። ኢራንቡቲ በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ የምትገኝ ውብ ሥፍራ ናት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!