መርጡለ ማርያም የማርያም አዳራሽ ማለት ነው

0
210

ከአዲስ አበባ 367 ኪሎ ሜትር እና ከባሕር ዳር 181 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ገዳም ናት በኢትዮጵያ መስዋዕተ ኦሪት ሲሰዋባቸው ከነበሩት አራቱ ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዷ ናት በሙሴ እንደመጡ የሚነገርላቸው እና በኦሪት ዘመን የነበሩ ባለ ስድስት ማዕዘን ድንጋዮችም በአምባው ተተክለው ይገኛሉ

በገዳሙ አስደናቂ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በቅርስነት ተጠብቆ ይገኛል የግማሽ ክብ ቅርጽ ያለው በአበባ እና ሐረግ የተጌጠ ሰፊ የበር አምድ፣ መስኮቶች፣ ከሕንጻው አናት ላይ የሚገኙ ከድንጋይ የተቀረጹ ሥዕለ ጽላት፣ ሥዕለ ኪሩብ እና ልዩ ልዩ ቅርጻ ቅርጾች በሕንጻው አብዛኛው ክፍል ከነውበታቸው ዛሬም ድረስ ይታያሉ

የሕንጻው አምዶችን እና መቅደሱ እጅግ በተዋበ የድንጋይ ሐረግ ቅርጽ ተጊጠው በወርቅ እና በዕንቁ ተውበው እንደነበረም ይነገራል።

ይቺን አስደናቂ ገዳም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጎብኝተዋታል። ከእርሳቸው አስቀድሞ የነበሩ ነገሥታትም ተመላልሰውባታም።

የአብርሃ ወአጽብሃ የወርቅ መስቀል፣ በ445 ዓ.ም የተጻፈ ግዕዙን በግዕዝ የሚተረጉም አርባዕቱ ወንጌል፣ የአጼ በእደ ማርያም ራስ ቁርና የወርቅ ለምድ፣ የንግሥት እሌኒ የክብር ካባና የብር ዋንጫ፣ የብርና የወርቅ መስቀሎች፣ የወርቅ አክሊሎች፣ የወርቅ ከበሮ፣ የአጼ ገላውዲዮስ ዳዊትና ካባ፣ የብራና መጻሕፍት እና ሌሎችም ይገኛሉ

የአካባቢውን ቱሪዝም ለማነቃቃት የክልሉ ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ ባለፉት ዓመታት “አስተርዮን በመርጡለ ማሪያም” በሚል መርሐ ግብር የማስተዋወቅ ሥራዎችን ሠርቷል።

መርጡለ ማርያም በበዓለ አስተርዮ ትደምቃለች።

ምንጭ፦ የአማራ ክልል ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here