ተናፋቂው የአሆላሌ የልጃገረዶች ጨዋታ በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ ተከበረ።

0
194

ባሕር ዳር: የካቲት 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ)የአሆላሌ ባሕላዊ ጨዋታ በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ ከሚገኙ ልዩ ልዩ ባሕላዊ ሁነቶች መካከል አንዱ ነው።

ክዋኔው በዋናነት በልጃገረዶች አቀንቃኝነት እና ተቀባይነት ይከወናል። ወጣት ወንዶችም በሆታ እና በጭፈራ ያጅቧቸዋል። በጨዋታው ሂደትም ወጣት ልጃገረዶች እና ወንዶች የራሳቸውን አለባበስ እና አጌያጌጥ ይጠቀማሉ። ወንዶቹ የተለያዩ ሥነ ቃሎችን እየተጠቀሙ ለልጃገረዶች ጨዋታ ድምቀት ይኾኗቸዋል።

ጨዋታውን በዓመት ሦስት ጊዜ እንደሚያከብሩት የአካባቢው ነዋሪዎች እና የክዋኔው ተሳታፊ ልጃገረዶች ይገልጻሉ።

የአሆላሌ ጨዋታ ባሕላዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች እና ተሳታፊዎች በተገኙበት “ባሕል የማንነት መገለጫ ነው፤ እንጠብቀው” በሚል መሪ ሃሳብ ትናንት በድምቀት መከበሩን የተሁለደሬ ወረዳ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here