የቅርሶች አምባ-ገነተ ማርያም!

0
97

ባሕር ዳር: መጋቢት 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ላስታ እና ቡግና በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ጎልተው ከሚታወቁ አካባቢያዊ ስሞች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

በወረዳዎቹ በተለያዩ ሥርዎ መንግሥታት ዘመን የተሠሩ በርካታ መካነ ቅርሶች እንደሚገኙ የአማራ ክልል ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ መረጃ ያሳያል።

ከላሊበላ ከተማ በቅርብ ርቀት ከሚገኙት እነዚህ በርካታ የመስህብ ቦታዎች መካከል ለዛሬው የቅርሶች አምባ – ገነተ ማርያምን እናስተዋውቃችሁ።

የገነተ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከላሊበላ ከተማ ወደ ወልዲያ በሚወስደው አማራጭ የጠጠር መንገድ 31 ኪሎ ሜትር ርቀት ትገኛለች፡፡

ቤተ ክርስቲያኗ በከፊል ውቅር ስትኾን በ1260ዎቹ በአጼ ይኩኖአምላከ ዘመነ መንግሥት እንደተሠራች ይነገራል።

የቤተ ክርስቲያኗ አብዛኛው ክፍል በጥንቃቄ ተፈልፍሎ ከቋጥኝ እና ገደል ነፃ ኾኖ ለብቻው የቆመ በመኾኑ ከላሊበላው ቤተ መድኃኒዓለም ጋር ያመሳስላታል፡፡

በዙሪያ የሚገኘው የተጠረበው ቋጥኝ ደግሞ እንደ አጥር የሚያገለግል ሲኾን በመግቢያው በር ግራ እና ቀኝ የመስቀል ቅርጽ ተቀርጾበታል፡፡

በሕንጻው ውስጥ ጥንታዊ የኢትዮጵያን ባሕላዊ የስዕል አሳሳል ስልት የተከተሉ የግድግዳ እና ጨርቅ ላይ የቀለም ቅብ እና የገበታ ላይ ስዕሎችም ይገኛሉ፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here