ደብረማርቆስ:ሚያዝያ 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ሚያዝያን በደብረማርቆስ በሚል ዓመታዊውን የቅዱስ ማርቆስ በዓል ለማስተናገድ እየተሠራ መኾኑን የከተማ አሥተዳደሩ ባሕል እና ቱሪዝም ተጠሪ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
በየዓመቱ ሚያዚያ 30 የሚከበረው የቅዱስ ማርቆስ የንግስ በዓል በርካታ ጎብኝዎችን ወደ ከተማዋ በመሳብ አስተዋጽኦ ሲያደርግ ቆይቷል።
በሀገር ውስጥ እና በውጭም የሚኖሩ ጎብኝዎች በየዓመቱ የሚታደሙበትን ዓመታዊ በዓል በድምቀት ለማክበር ዝግጅት መደረጉን የከተማ አሥተዳደሩ ባሕል እና ቱሪዝም ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ የውልሰው ወርቅነህ ገልጸዋል።
በበዓሉ ሃይማኖታዊ እሴትን ከማስጠበቅ ባሻገር ታሪካዊ ቅርሶችን መመልከት፣ ታሪክን መረዳት እና የሀገርን ባሕል ብሎም ወግ ለማስቀጠል ዕውቀት የሚገኝበት እንደኾነም ኀላፊዋ አስገንዝበዋል።
በበዓሉ ለመታደም ለሚመጡ እንግዶች ማረፊያ ቦታ የተዘጋጀ መኾኑንም ጠቁመዋል።
ኅብረተሰቡም በዓሉን ለማክበር ለሚመጡ እንግዶች በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ተቀብሎ እንዲያስተናግድም መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሚያዚያ 30/2017 ዓ.ም የቅዱስ ማርቆስ ዓመታዊ ንግስ የሚከበርበት እና ሃይማኖታዊ ዝግጅቶች የሚቀርቡበት እንደሚኾንም ተብራርቷል።
በዓሉ በድምቀት እንዲከበር እና በሰላም እንዲጠናቀቅ ኹሉም አካል የድርሻውን እንዲያበረክትም ጥሪ ቀርቧል።
በዓሉ ከሚያዝያ 27/08/17 ጀምሮ ይከበራል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን