“አንዲት ግራር” የሸዋ አናብስት አሻራ!

0
78

👉በፋሽስት ኢጣልያ ወረራ ጊዜ በነበረ የአርበኝነት ተጋድሎ ጉልህ ስፍራ የሚሰጣት አንዲት ግራር ነች
👉በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የአርበኞች ማኅበር የተመሰረተባት ታሪካዊ የጀግንነት አሻራም ነች
👉በሰሜን ሸዋ ዞን በሞጃና ወደራ ወረዳ እንግዳ ዋሻ ቀበሌ አንቀላፊኝ ሜዳ በተባለች ስፍራ ላይ ትገኛለች
👉”አንዲት ግራር” የሚል ስያሜ የተሰጣት በአካባቢው አንድና ብቸኛ የግራር ዛፍ መገኛ ስለነበረች ነው
👉ወራሪዎችን ድል ለማድረግ የጦርነት ስልታቸውን መቀየር ነበረባቸው እና በዱር በገደሉ የነበሩት የጦር አለቆች ያስከተሉትን ጦር በመያዝ ጥር 1 ቀን 1931 ዓ.ም በባላንባራስ ባሻህ ኃይሌ ሰብሳቢነት “አንዲት ግራር” ከግራሯ ስር ተሰባስበው ተወያዩ
👉በዚች ዛፍ ስር ባደረጉት ምክክር ኅብረታቸውን ፈጠሩ፤
👉ዳግም ላለመሸነፍ እና ወደ ኋላ ላለመመለስም ቃለ መሃላ ፈጸሙ
👉አባቶቻችንና እናቶቻችን ደማቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን ከስክሰው ያስገኙት ድል በመሆኑ መጪው ትውልድ ታሪኩን እንዲያውቅ ማድረግ ይገባል
👉አርበኞቻችን በወረራው ጊዜ ያሳዩት ጀብድ ለአሁኑ ትውልድ ምሳሌ ነው
👉የሁሉ መሰረት የሆነውን ሰላም መገንባት፣ መንከባከብና ሰላምን ሊያሳጡ የሚችሉ ነገሮች ሲታዩ ለመፍታት መረባረብ ይገባል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here