አንኮበር እና ቤተ መንግሥቷ!

0
142

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) አንኮበር ከደብረ ብርሃን ከተማ በስተምሥራቅ አቅጣጫ በ42 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡

የአንኮበር ወረዳ ባሕል እና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት መረጃ እንደሚያስረዳው ከአጼ ይኩኖአምላክ (ከ1262 ዓ.ም እስከ 1277 ዓ.ም) ጀምሮ ለኢትዮጵያ ነገሥታት ማረፊያነት ያገለገለችው አንኮበር አጼ አምደጽዮን የድንኳን ከተማቸውን እንደተከሉባት፤ አጼ ልብነድንግል ደግሞ በተሻለ ሁኔታ የባለወልድ ቤተ ክርስቲያንን ለማነጽ ጀምረው እንደነበር ታሪክ ያሳያል፡፡

የከተማነት ታሪኳ የጎላው ግን የሸዋ ሥርወ መንግሥት በመንዝ በማንሠራራት (ከ1665 ዓ.ም እስከ 1881 ዓ.ም) የመስፋፋት እንቅስቃሴ በጀመረበት ወቅት እንደኾነ መረጃው ያሳያል፡፡

የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ወደ እንጦጦ እስከዞረበት እና በኋላም አዲስ አበባ እስከተቆረቆረችበት ጊዜ ድረስ በቀዝቃዛ አየሯ የምትታወቀው አንኮበር ለስድስት የሸዋ ነገሥታት በማዕከልነት አገልግላለች።

የሸዋ ነገሥታት ቋሚ መናኸሪያ ለመኾን የበቃችው ግን በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሥልጣን በያዙት በንጉሥ ሳህለ ሥላሴ (ከ1806 ዓ.ም እስከ 1840 ዓ.ም) ነበር፡፡

አንኮበር በታሪክ ሂደት ቤተ መንግሥት እና በርካታ ታሪካዊ አብያተ ክርስቲያናትም ተሠርተውባታል፡፡ የአንኮበር ቤተ መንግሥት ለዚህ ተጠቃሽ ነው፡፡

ቤተ መንግሥቱ በ1830 ዓ.ም በንጉሥ ሳህለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት የተሠራ ሲኾን ዳግማዊ ምኒልክም ቤተ መንግሥታቸውን ወደ እንጦጦ ከመቀየራቸው በፊት ሸዋን አሥተዳድረውበታል፡፡

በአሁን ሰዓት ቤተ መንግሥቱ እንደገና ተገንብቶ የሎጅ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ በቤተ መንግሥቱ የንጉሥ ሳህለ ሥላሴ እልፍኝ ፍርስራሽን ጨምሮ በርከት ያሉ ቅርሶችም ይገኙበታል፡፡

በደመወዝ የቆየ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here